Others
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ሃገራዊ ምርጫ ቀሪና ድጋሚ ምርጫ ለማስፈፀም ስልጠና እና የኦፕሬሽን ቁሳቁስ ስርጭት ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ፣ ፎርክሊፍት፣ የሰራተኛ ሰርቪስ እና የከተማ ውስጥ ጭነት የኪራይ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር NEBE/NCB/02/2019
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ሃገራዊ ምርጫ ቀሪና ድጋሚ ምርጫ ለማስፈፀም ስልጠና እና የኦፕሬሽን ቁሳቁስ ስርጭት፣ ፎርክሊፍት፣ የሰራተኛ ሰርቪስ እና የከተማ ውስጥ ጭነት የኪራይ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
- ምድብ አንድ፡- ለቀሪና ድጋሚ ምርጫ አስፈላጊ የሆኑ የስልጠናና ኦፕሬሽን ቁሳቁስ ስርጭት ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ
- ምድብ ሁለት- ፎርከሊፍት፣ የሠራተኛ ሰርቪስ፣ እና የጭነት ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ
- ምድብ ሦስት:- በዋናው መ/ቤት የሚከናወኑ ስራዎችን ለማከናወን እና ለሠራተኞች ሰርቪስ የሚሰጡ ደብል ጋቢና ፒክአፕ እና 14 ሰው የመጫን አቅም ያለው መካከለኛ ባስ ኪራይ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም
1. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ባሉት የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ከቦርዱ ግዥ ስራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 107 ማግኘት ይችላሉ።
2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሠርተፍኬት፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሠርተፍኬት እና በመንግስት ኤሌክትሮኒክስ ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ ስለመሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. ተወዳዳሪዎች በሚወዳደሩበት መስክ ያላቸውን መልካም አፈጻጸም የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. የጨረታ ሰነዱን ከቦርዱ የግዥ አስተዳደር የሥራ ክፍል በመውሰድ ሞልተው አግባብ ባለው አካል በመፈረም ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ፡-
- ለምድብ አንድ ብር 100,000.00 (ብር አንድ መቶ ሺህ ከ00/100)
- ለምድብ ሁለት ብር 100,000.00 (ብር አንድ መቶ ሺህ ከ00/100)
- ለምድብ ሦስት ብር 50,000.00 (ብር ሃምሳ ሺህ ከ00/100) በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
6. ተወዳዳሪዎች ቴክኒካል ፕሮፖዛል እና ፋይናንሻል ፕሮፖዛል በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
7. ጨረታው መስከረም 04 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
8. ቦርዱ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
አድራሻችን፡- ቦሌ ፍላሚንጎ ሬስቶራንት ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡- +251 115 153 468
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
Tender details
- Deadline: 2026-09-14
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-09-14 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: National Election Board of Ethiopia
- Buyer address: ቦሌ ፍላሚንጎ ካፌ ገባ ብሎ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 26, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T13:30:10.000Z