Textile, Garment and Leather
የኮልፌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም
የኮልፌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1-የደንብ ልብስ ግዥ እና የስፌት አገልግሎት ፤
- ሎት.2 አላቂ የቢሮ እና የትምህርት ዕቃዎች፤
- ሎት.3-ህትመት
- ሎት.4-አላቂ ህክምና ዕቃ
- ሎት 5-ለአላቂ ፅዳት ዕቃዎች
- ሎት.6-ልዩ ልዩ አጋዝ መፅሀፍቶች በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት
- ሎት.7- ቋሚ ዕቃዎች ፤
- ሎት.8-የተለያዩ የጥገና ስራዎች እና ዕቃዎች
- ሎት.9 የጄኔሬተር ጥገና እና ዕቃ የፕሪንተሮች እና ፎቶ ኮፒ የማባዥ ማሽኖች ሰርቪስ (የቢሮ ዕቃዎች ጥገና)፤
- ሎት10-የመኪና ጥገና፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች
- ሎት11- ለቤተ ሙከራ የሚሆኑ ኬሚካሎች ዕቃዎች
- ሎት 12-ቆሎ እና ኩኪስ
- ሎት13- የመኪና ኪራይ አገልግሎት
- ሎት-14 ለመምህራን እና ሰራተኞች ካፌ አገልግሎት ስራ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ
በተጫራቾች መመሪያ
1. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ከአገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን የዘመኑ የመንግስት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ እንዲሁም የአቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃዎች የሚሸጡበትን የአንዱን ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ በመግልጽ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን እና የጨረታ ዓይነት በግልፅ በመጻፍ እንዲሁም ተሞሉቶ የዋጋ ዝርዝር ጋር መደበኛ የጨረታ ሰነዱ ሙሉ በሙሉ መመለስ አለበት፡፡ የጨረታ ሰነዱ ካልተመለሰ የጨረታ ውድድሩ ላይ መቅረብ የማይችሉ መሆኑን እየገለፅን በአግባቡ የተሞላውን የጨረታ ሰነድ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የኮልፌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ/ግ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 የጨረታ ሳጥን መግባት ይኖርበታል።
3. ተጫራቾች ሙሉ በሙሉ ስማቸውን ፤ አድራሻቸውንና ፤ ፊርማቸውን በእያንዳዱ ሰነድ ላይ በመፈረም ማቅረብ አለባቸው ሰነዶቹ በማህተም መረጋገጥ አለባቸው፡፡
4. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት እቃዎችን ከግዥ አስተዳደሩ ጋር በሚገባው ውል መሰረት እንዲያስገባ ሲታዘዝ እቃ ግምጃ ቤታችን ድረስ በራሱ ወጪ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
5. አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ እቃዎች ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
6. ማንኛውም ተጫራች የመ/ቤቱ የእቃ ጥራት ተቆጣጣሪ ኮሚቴ የእቃዎችን ጥራት አይቶ መ/ቤቱ ካወጣው የጨረታ ሰነድ እና በጨረታው እንዲያልፍ ከተደረገው የእቃ ቴክኒካል ስፔስፊኬሽንና ከቀረበው ናሙና ጋር የማይጣጣም ከሆነና ጥራት የጎደለው ነው ብሎ ካመነ ጨረታውን አሸንፎ እቃ እንዲያቀርብ የታዘዘው/ድርጅት እቃውን እንዲመልስ ማድረግ ይችላል።
7. በጨረታው ያሸነፈ አካል ማሸነፍ እንደተገለፀለት ከመ/ቤቱ ጋር በ15 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መፈፀም አለበት፡፡
8. የግዥ ውል የሚፈፀምበት ጊዜ ሰነዱ ላይ የተሰጠው የእቃ ብዛት በተወሰነ መጠን ሊጨምርም ወይም ሊቀንስ የሚችል መሆኑን ተጫራቹ አውቆ የመጫረት ግዴታ አለበት፡፡
9. ተጫራቾች ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ቀደም ብለው ለሚጫረቱባቸው እቃዎች ናሙና ቢሮ ቁጥር 6 ማስረከብ አለባቸው፡፡
10. የሚሸጠው የጨረታ ሰነድ የማይመለሰ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ መክፈል ይኖርበታል፡፡
11. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
12. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
13. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
14. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የተጠቀሰውን ብር ከታወቀ ባንክ በcpo አሰርታችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ የእያንዳንዱ ሎት በጀትን የተሰላው በ0.5% ነው።
15. የጥቃቅን እና አነስተኛ ተወዳዳሪዎች የሚያመርቱትን ምርት የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
|
ሎት-1 |
ሎት-2 |
ሎት-3 |
ሎት-4 |
ሎት-5 |
ሎት 6 |
ሎት-7 |
ሎት-8 |
ሎት-9 |
ሎት-10 |
ሎት-11 |
ሎት-12 |
ሎት-13 |
ሎት-14 |
|
12400 |
18800 |
1500 |
1000 |
12000 |
1000 |
1400 |
4000 |
2400 |
1500 |
1100 |
1000 |
2400 |
11000 |
ለበለጠ መረጃ አድራሻ
ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 በ18 ሉኳንዳ ወደ አሸዋ ሜዳ በሚወስደው መንገድ ይገኛል፡፡
ስልክ ቁጥር 0112 790 012 / 0112 592 157
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምርህርት ቢሮ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የኮልፌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-07
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛ ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-07 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛ ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Kolfe General Secondary School
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 26, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T13:36:38.000Z