Catering and Cafeteria Services

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለሀዋሳ ኤርፖርት ፓይለት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት (PTSC) ካፌቴሪያ አገልግሎት የሚውል የስጋ ምርት አቅራቢ ድርጅቶች ጋር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ስምምነት ለሶሥት (3) አመት ለመስራት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: SSNT-T637

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለሀዋሳ ኤርፖርት ፓይለት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት (PTSC) ካፌቴሪያ አገልግሎት የሚውል የስጋ ምርት አቅራቢ ድርጅቶች ጋር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ስምምነት ለሶሥት (3) አመት ለመስራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ በአገልግሎቱ ዘርፍ ለመሠማራት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው ፤ ለ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፊቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ምዝገባ ወረቀት ያለው፣የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ ፣ ሁለት (2) ዓመትና እና ከዚያ በላይ የሰራ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ሁለት መቶ ብር (ብር 200.00) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T637 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ቅጂውን (scan copy) በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሀምሳ ሺህ ብር (50,000.00) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ ተቋም እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን እና የጨረታ ማስከበሪያ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ መስከረም 06 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየርመንገድ ዋና መስሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ:
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መስሪያ ቤት ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ስልክ ቁጥር፡ 011-517-4552
አሊ አስፋው
ኢ-ሜይል: [email protected] 
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::


Tender details

  • Deadline: 2026-09-16
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid opening: 2026-09-16 15:30
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
  • Buyer TIN: 0000028498
  • Bid bond: (50,000.00) ሀምሳ ሺህ ብር
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 26, 2026)
  • Posted at: 2026-08-26T14:05:19.000Z
← Back to all tenders