Catering and Cafeteria Services
የአ/ምንጭ ልዩ ፍላጎት ትም/ቤት በ2019 ዓ.ም ቁርስና ምሳ ለማቅረብ ምግብ ቤቶችን እና ቁርስ ቤቶችን በጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ማሠራት ይፈልጋል
Description
የአርባ ምንጭ ልዩ ፍላጎት ት/ ቤት ማስታወቂያ
የአ/ምንጭ ልዩ ፍላጎት ትም/ቤት በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለሚያስተምራቸው አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ጨረታ በሲቀላና ሼቻ ለሚገኘው ልዩ ት/ቤት ተማሪዎች ከመስከረም 4/1/2019 ዓ.ም እስከ 30/10/209 ዓ.ም ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ ድረስ በሥራ ቀናት ቁርስና ምሳ ለማቅረብ በቁርስ ቁርስ ፍቃድ ያለው እና በምሳ አገልግሎት ፍቃድ ያለው ማንኛውም ተጫራች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መወዳደር ይቻላል የቁርስና የምሳ አገልግሎት በተወሰነው ሰዓት ውስጥ እስከ ት/ቤታችን ድረስ አዘጋጅተው በማቅረብ መመገብ የሚችሉና በበሰለ ምግብ አቅራቢነት ተመዝግበው በጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ተደራጅተው የሚሠሩ ምግብ ቤቶችን ቁርስ ቤቶችን በጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ማሠራት ይፈልጋል።
በመሆኑም፦
1. ከዞኑ ፋይ/ኢ/ል/ማ ቢሮ በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገበበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ 1. በጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት የተደራጁ።
2. ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ኦርጂናልና አንድ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ/የሚችል።
3. የጨረታ ማስከበሪያ ቢድቦንድ 3000.00 /ሶስት ሺህ/ ወይም የባንከ ሲ.ፒ.ዩ (cpo) ማቅረብ የሚችል።
4. ቢቻል በዚህ ተመሳሳይ ሥራ የሠራበትን የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚችል።
5. የጨረታ ሰነዱን ከአ/ምንጭ ልዩ ትም/ቤት የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት የሚችል።
6. ተጫራቾች የምግብ ዓይነቱን ዝርዝር ከ20/12/2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 3/13/2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን ከት/ቤቱ በመግዛት ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከ2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይኖርበታል።
7. በ3/13/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ይታሸጋል። ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይታሸጋል።
8. የጨረታ ሳጥን በ4/13/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ሕንፃ ቁጥር 1 ክፍል 1 ይክፈታል።
9. ተጫራቾች ያስያዙት ቢድ ቦንድ አሸናፊው እንደታወቀ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆንላቸዋል።
10. ከተጠናው የገበያ ዋጋ በጣም ዝቅተኛና አውርዶ ማቅረብ ከምግብ ጥራት አኳያ ስለሚታይ ተጫራቾች በጥንቃቄ ሰነዱን መሙላት ይኖርባቸዋል።
11. ትም/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በመሉም ሆነ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. የጨረታው አሸናፊ የውል ማስከበሪያ የዓመቱን ጠቅላላ ሂሣብ 1ዐ% በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል።
13. የጨረታ ማስከበሪያ ቢድቦንድ ያላስያዘ ተጫራች ቢቀርብ ተቀባይነት የለውም።
14. ተጫራቾች ሰነዱን ለመግዛት ሲቀርቡ ኦርጂናል የንግድ ማስረጃቸውን አቅርበው መመዝገብ አለባቸው።
15. የዋጋ ማቅረቢያ በተለየ ፖስታ ታሽጎ በላዩ ላይ ስም ተጽፎበት ማህተም ተደርጎ መቅረብ አለበት።
16. ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር፡-046 881 1929
ሞባይል 09 16 52 09 43 መረዳት ይችላል።
የአርባ ምንጭ ልዩ ፍላጎት ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-08
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-09-09 10:00
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Arba Minch Special Need School
- Bid bond: 3000.00 (ሶስት ሺህ ብር)
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Aug 28, 2026)
- Posted at: 2026-08-28T07:54:16.000Z