Materials

የቢሾፍቱ ፖሊ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ለ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት በኮሌጁ ውስጥ ለሚገኙት ለተለያዩ ዲፓርትመንቶች ለማሰልጠኛ የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የቢሾፍቱ ፖሊ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ለ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት በኮሌጁ ውስጥ ለሚገኙት ለተለያዩ ዲፓርትመንቶች ለማሰልጠኛ የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡።

3. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በሌላም የሚመለከታቸው ፍቃድ ሰጪ አካል አቅራቢዎች የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መካፈል ይችላሉ።

4. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፉአቸውን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት አቅርቦት ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት።

5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የሚጫረቱበትን የማይመለስ ብር 600 (ስድስት መቶ ብር)በ Siinqee Acc, 1064859701215 በመክፈል የBank ስሊፕ ይዘው የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በቢሾፍቱ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የፋይናንስ አስተዳደር የስራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

6. ኮሌጃችን የሚያጫርታቸውን እቃዎች ብዛት እንደ አስፈላጊነታቸው መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ CPO ብቻ የምንቀበል መሆኑን በማወቅ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) የጨረታ ሰነዱን ሲያስገቡ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

8. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒውን በማመሳከር ለየብቻ በማሸግ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት ከላይ የቢሾፍቱ ፖሊ ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ በመቅረብ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ወዲያውኑ በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሾፍቱ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የፋይናንስ አስተዳደር የስራ ሂደት ይከፈታል።

10. ኮሌጁ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. በSpecification ላይ መሰረዝ መደለዝ የራስን ሃሳብ መጨመር አይቻልም።

አድራሻ፡- የቢሾፍቱ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ 09 12 95 94 24 / 09 19 32 36 48

በኦሮሚያ የስራ ዕድል ፈጠራ እና ክህሎት ቢሮ የቢሾፍቱ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-15
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-15 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከሰዓት በኋላ በ8፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Bishoftu Poly Technic College
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 600.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 28, 2026)
  • Posted at: 2026-08-28T08:55:58.000Z
← Back to all tenders