Textile, Garment and Leather

ትግል ለነፃነት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ለትግል ለነፃነት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ትለ፤ 001/2019 ዓ.ም.

1ኛ/ የደንብ ልብስና የወንድ እና የሴት ጫማዎች

2ኛ/ አላቂ የፅዳት ዕቃዎችን

3ኛ/ የትምህርት የፅህፈት መሳሪያዎችን

4ኛ/ የቢሮ አላቂ ዕቃዎች

5ኛ/ የስፖርት ትጥቆች እና የስፖርት ዕቃዎች

6ኛ/ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች

7ኛ/ የህንፃ መሳሪያዎች

8ኛ/ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፣ የቫት የምዘገባ ወረቀት አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

1. ያሸነፉበትን ዕቃ ግዥ መ/ቤት ድረስ በራሳቸው ወጭ ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች የአንዱን ዋጋ ሲያቀርቡ ከነቫቱ ደምረው ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ/ ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት አለባቸው ፡፡ ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ በመ/ቤቱ ሰነድ ብቻ መሆን አለበት።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ማስገቢያ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ለተከታታይ ለ10 የስራ ቀናት ይሆናል።

5. ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ዕቃዎችን ማስረከበ ያለበት ማሸነፉን ከተነገረው በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ማስረከብ አለባቸው።

6. የጨረታው ማስገቢያ ት/ቤት ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት።

7. የጨረታውን ሰነድ ከላይ በተራ ቁጥር 4 የተጠቀሰውን ገንዘብ በመክፈል በት/ቤቱ ፋይ/ግ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 መውሰድ ይቻላል።

8. ጨረታው በወጣ በአስራ አንደኛው ቀን 4:15 /አራት ሰዓት ከሩብ/ ታሽጎ 4:30 /አራት ሰዓት ተኩል/ት/ቤቱ አዳራሽ ህጋዊ ተጫራቾቻቸው ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል ።

9. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱን የተጠበቀ ነው።

ለጨረታ ማስከበሪያ ብር ከታች የተገለፀውን በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት።

የደንብ ልብስና የወንድና የሴት ጫማዎች ብር 3000/ሶስት ሺህ/፣ የአላቂ የፅዳት ዕቃዎች ብር 6000 /ስድስት ሺህ ብር/፣ የትምህርት እና የፅህፈት መሳሪያዎች ብር 5500/አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር/ የቢሮ አላቂ ዕቃዎች በብር 5500/አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር / ፣የስፖርት ትጥቆች እና የስፖርት ዕቃዎች ብር 4000/አራት ሺህ/፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ብር 4000/አራት ሺህ/ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች ብር 4500/አራት ሺህ አምስት መቶ/ ፣የህንፃ መሳሪያዎች ብር 4500 /አራት ሺህ አምስት መቶ/ እንዲሁም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 4000/አራት ሺህ ብር/።

አድራሻ፡- ትግል ነፃነት ቅድመ አንደኛና አንደኛ መካከለኛ ደረጀ ትምህርት ቤት በየካ ክፍለ ከተማ በቀድሞ ቀበሌ 01/02በአዲሱ ወረዳ 01 ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ሳይደርስ 800 ሜ ሲቀረው 41 ቁጥር አውቶቢስ መሄጃ መስመር

ማሳሰቢያ፦ ለጥራት 80% ለዋጋ 20% ስለሆነ ለጥራት ከምንም በላይ ቅድሚያ እንሰጣለን።

  • የአንዱን ዕቃ ዋጋ ስታቀርቡ ከነቫቱ ማቅረብ አለባችሁ።
  • ቫት ሳያካትት ዋጋ ያቀረበ ድርጅት ጨረታው ወድቅ ይሆንበታል።
  • ማንኛውንም ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ ሲያስገባ ሳምፕል ማቅረብ አለበት።
  • ማንኛውም ተጫራች መረጃ መጠየቅ ሲፈልግ በስራ ቀናት ጠዋት 2፡30-11፡30 ባለው ጊዜ ደውሎ መረጃ መጠየቅ ይችላል:: ቅዳሜና እሁድ የእረፍት ቀናት ስለሆነ መ/ቤቱ ዝግ ነው።

ስልክ ቁጥር፡-0111 541 611 / 0118 120 047

የትግል ለነፃነት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-09
  • Bid closing time: 10:15
  • Bid closing (note): ጨረታው በወጣ በአስራ አንደኛው ቀን 4:15 /አራት ሰዓት ከሩብ/
  • Bid opening: 2026-09-09 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በወጣ በአስራ አንደኛው ቀን 4:30 /አራት ሰዓት ተኩል
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Tigil Lenetsanet Kindergarten, Elementary and Middle School
  • Buyer address: ትግል ለነፃነት አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የካ ክፍለ ከተማ በቀድሞ ቀበሌ 01/02 በአዲሱ ወረዳ -01 እየሱስ ቤተክርስቲያን ሣይደርስ 800 ሜ ሲቀረው 41 ቁጥር አውቶብስ መሄጃ መስመር
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 28, 2026)
  • Posted at: 2026-08-28T09:10:06.000Z
← Back to all tenders