House Furniture

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በምዕራብ አርሲ ዞን የሲራሮ ወራዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳ ለሚገኙ ሴከተር መ/ቤቶች የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በምዕራብ አርሲ ዞን የሲራሮ ወራዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳ ለሚገኙ ሴከተር መ/ቤቶች 1ኛ ዙር ግዥ ለ1 ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ሰነድ በ2019 የበጀት ዓመት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ማለትም ፡-

  • አላቅ ዕቃዎች /ጽህፈት መሳሪያዎች
  • ኤሌትሮኒክስ
  • ፈርኒቸር
  • የፅዳት ዕቃዎች
  • የደንብ ልብስ

ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጸውን በግልጽ ጨረታ ህጋዊና አቅም ያላቸውን ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

መመሪያ/ መስፈርት በመከተል ይህን ጨረታ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።

1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን 2018/2019 ግብር የከፈሉ እንዲሁም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ቫት ከፋይ የሆኑ TIN Number ማቅረብ የሚችሉ

2. ማንኛውም ተጫራች ወደ ጨረታው ሂደት ከገባ በኋላ በሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውንም ሁኔታዎች ማሻሸል መቀየር እንዲሁም ሀሳቤን ቀይሬአለው ማለት አይቻልም።

3. ማንኛውም ዕጩ ተወዳደሪ የጨረታውን ሂደት ለማስተጓጐል ቢሞከር ከጨረታው ውጭ እንዲሆን ተደርጎ ወደ ፊት በሚደረገው የመንግስት ግዥ ላይ እንደይሳተፍ የሚደረግ እና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ የሚሆን ይሆናል።

4. ማንኛውም ተጫራች በመንግስት ግዥ ለመሳተፍ እንዲችል የሚገልጽ ከህጋዊ አካል የተሰጠ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት።

5. ተጫራቾች በሚሰሩበት የንግድ እና በንግድ ፍቃዳቸው ዘርፍ ብቻ ነዉ መወዳደር የምትችሉት።

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለያንድአንዱ የግዥ መደብ ብር 5000/አምስት ሺህ ብር ብቻ, በባንክ በተመሰከረለት CPO ማቅረብ አለበት፡፡ ነገር ግን በካሽ ከሆነ በሲራሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መደበኛ ሂሳብ ቁጥር 1000289568418 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ ተደርጎ computer generated slip መቅረብ አለበት።

7. ተወዳዳሪ ድርጅቶች የዕቃ ጥራት ደረጃቸው አስቸጋሪ የሆኑ የዕቃ ዓይነቶች መሥሪያቤታችን ቀድሞ ስላዘጋጃ ለምሳሌ የኮምፒተር ወረቀት፣ እስክሪብቶዎች፣ኬንት፣ሶፍት፣ኡሁ የኮምፒተር ቀለም፣ ኦርጅናል የቆዳ ወጤቶች ፣ቦርሳዎች እና ሌሎችም ተወዳዳሪ ድርጅቶች ይህን ናሙና መሠረት በማድረግ ብቻ የምንቀበል መሆኑን በጥበቅ እናሳስባለን።

8. አሸናፊ ድርጅት ዕቃዉን ጭነዉ እስከ መ/ቤታችን ግምጃ ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት።

9. ተጫራቾች ዕቃው የተሰራበትን የተመረተበትን ሀገርና የጥራት ደረጃ የመስራት አቅሙን እንዲሁም ሞዴሉንና የተመረተበትን ዓ.ም መግለጽ አለባቸው።

10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኮፒና ኦርጂናል በተለያዩ ፖስታ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸዉ።

11. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋውን መሙላት ያለባቸው በተሸጠላቸው ሰነድ ላይ ብቻ መሆን አለበት ፡፡ እንዲሁም እያንዳንዱ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡ በራሳቸዉ ሰነድ ላይ የሚሞላ ለስራችን አመቺ ስለማይሆን ተቀባይነት የለውም።

12. ጽ/ቤታችን የሚያጫርታቸውን የአንዱ ዋጋ ሲሆን አሸናፊው የሚፈልገውን የዕቃ ብዛት ማዘዝ ይችላል።

13. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ስልክ ቁጥራቸውን ፋክስ ቁጥራቸውን በትከክል ፅፈዉ መፈረምና ማህተም ማድረግ አለባቸው።

14. ተወዳዳሪዎች የሚሰጡት የጨረታ ዋጋው ጨረታዉ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ 60 ቀናት ወይም ሁለት ወር ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት።

15. መ/ቤቱ ጨረታውን ገምግሞ ለማሳለፍ ወይም ውድቅ ለማድረግ የሚጠቀምበት ዘዴ እንደ ዕቃው አይነት ወይም የሚፈለገዉ አገልግሎትን መሰረት በማድረግ ጥራትን ወይም ዋጋን ከግንዛቤ በማስገባት ተወዳዳሪዎችን አሸናፊ ወይም ውድቅ የሚያደርግ ሲሆን ሁለት እኩል ዋጋ ቢያቀርቡ በብዘት ላሸነፈው የሚሰጥ ይሆናል።

16. የሰነዱ ሽያጭ የሚቆይበት ቀን 22/12/2018 እስከ 25/01/2019 ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ 26/01/2019 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ተዘግቶ ተጫራቹ ወይም ህጋዊ ወኪሉ በተገኘበት በዛው እለት 4፡30 ሰዓት ላይ በስራሮ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 ይከፈታል።

17. የጨረታ ሰነዱ ዝርዝር በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በስራሮ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ፅ/ቤት ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በየስራሮ ወረዳ ገንዘበ ፅ/ቤት በባንክ መደበኛ ሂሳብ ቁጥር 1000289568418 በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ገቢ በማድረግ ስሊፕ በመያዝ ቢሮ ቁጥር 07 ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን ተወዳዳሪ ድርጅቶች ሰነድ ከገዙበት ቀን ጀምሮ በተዘጋጀለት የጨረታ ሳጥን ውስጥ በስራ ሰዓት የሰነዱን ሽያጭ እስከሚያበቃበት ቀን ድረስ ማስገባት ይችላል።

18. የጨረታ ውል ከጨረታ ሰነድ ጋር ስለሚሸጥ በውል መሰረት ጨረታውን ያሸነፈው ነጋዴ ለውሉ ተገዥ መሆን አለበት።

19. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ከገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

20. አሸናፊ ድርጅቶች ካሸነፋ ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ መደበኛ ሂሳብ ቁጥር 1000289568418 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ ስሊፕ በመያዝ ወይም በተመሰከረለት CPO ማቅረብ አለበት።

ለበለጠ መረጃ ሞባይል 0994 442 023 / 0911 140 912

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ አርሲ ዞን የሲራሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-06
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-06 10:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: West Arsi Zone Siraro Woreda FEDB
  • Bid bond: 5,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 28, 2026)
  • Posted at: 2026-08-28T09:24:10.000Z
← Back to all tenders