Catering and Cafeteria Services

በአዲስ አበባ ከተማ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የአብዲ ጃርሶ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም ለት/ቤት የሰራተኞች የካፌ አገልግሎት አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የአብዲ ጃርሶ ት /ቤት ለ2019 ዓ.ም ለት/ቤት የሰራተኞች የካፌ አገልግሎት አወዳደሮ ለማስራት ይፈልጋል፡፡

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያማሉ ተወዳደሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

1/ በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ከሀገር ውስጥ የገቢዎች ባለስልጣን የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃቸውንና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆኑ የምስክር ወረቀትና ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2/ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ በተጨማሪም ካሽ ሪጅስተር ማሽን/ ደረሰኝ ያላቸው

3/ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለአስር/10/ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 እብዲ ጃርሶ ፋይናንስ ት/ቤት ዘወትር /2:30-11:30/ በስራ ሰዓት ሰነዱን 300 ብር መግዛት ይችላሉ፡፡

4/ ዋጋ በምታቀርቡበት ጊዜ ቫትን ያካተተ/ TOT/ መሆን አለበት።

5/ ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በለሚ ኩራ ከ/ከተማ ወረዳ 06 አብዲ ጃርሶ ፋይናንስ ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲሆን ጨረታው ከወጣበት በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን የሚከፈት ይሆናል።

6/ ተጫራቾች ያሸነፉበት ማንኛውንም የመስተንግዶ አገልግሎት ማቅረብ /መስጠት/ ይኖርባቸዋል።

7/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር /10,000/ አሥር ሺህ ብር/በባንክ የተመሰከረለት የከፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው። የማወዳደሪያ እቃውን ከቫት ጋር ደምረው ይላኩልን፡፡

8/ ካፌው በት/ቤቱ በተዘጋጀ ቦታ የሚሰጥ ይኖርባቸዋል፡፡

9/ መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ለሚኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 እብዲ ጃርሶ ፋይናንስ ት/ቤት ልዩ ስሙ ቦሌ አራብሳ ጃርሶ ገባ ብሎ።

የአብዲ ጃርሶ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትቤት

የአብዲ ጃርሶ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-07
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): የጨረታ ሰነድ ለአስር/10/ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ዘወትር /2:30-11:30/ በስራ ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-08 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን የሚከፈት ይሆናል
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: አብዲ ጃርሶ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Bid bond: 10,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 28, 2026)
  • Posted at: 2026-08-28T09:26:11.000Z
← Back to all tenders