Spare Parts and Car Decoration Materials

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን የ2019 በጀት ዓመት የኤሌክትሪክ መኪና ክራይ፣ የመኪና ቻርጀር ገመድ፣ የህትመት (ባነር፣ የስም ተተር፡ መታወቂያ፣ የደረት ባጅ፣ የጠረጴዛ ባጅ፣ ሮል ሀፕ፣ ስቲከር፣ መጽሀፍ ዝግጅት፣ በራሪ ወረቀቶች፤ የምስጋና የምስክር ወረቀት፣ የሽልማት ዋንጫ፣ በተለያየ) የመኪና ክራይ፣ ዲኮርና ድንኳን፣ ዲጄ፣ ቋሚ ፈርኒቸር እቃ፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃ፣ የደንብ ልብስ፣ የመኪና ጌጣጌጥ፣ ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ እቃ፣ የወጥ ቤት እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የሎት ቁጥር

የግዥ ዓይነት ዝርዝር /ሎት

የጨረታ ማስከበሪያ መያዣ /CPO/

1

የመኪና ቻርጀር ገመድ

50,000 /ሃምሳ ብር/

2

ህትመት

10,000 /አስር ብር/

3

የመኪና ክራይ

 

4

ዲኮርና ድንኳን

10,000 /አስር ብር/

5

ዲጄ

10,000 /አስር ብር/

6

ቋሚ ፈርኒቸር እቃ

50,000 /ሃምሳ ብር/

7

የጽህፈት መሳሪያ

10,000 /አስር ብር/

8

የጽዳት እቃ

10,000 /አስር ብር/

9

የደንብ ልብስ

10,000 /አስር ብር

10

የመኪና ጌጣጌጥ

50,000 /ሃምሳ ብር/

11

ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ እቃ

50,000 /ሃምሳ ብር/

12

የወጥ ቤት እቃዎች

10,000 /አስር ብር/

13

የኤሌክትሮኒክስ ጥገና

10,000 /አስር ብር/

ማሳሰቢያ:-

  • ተጫራቾች በዘርፉ የተመዘገቡበትን የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የንግድ ስም
  • ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
  • ከብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺ/ በላይ ለማቅረብ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የቫት /VAT/ ተመዝጋቢ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች የሚያቀርቧዋቸው ሰነዶች ሁሉ ተነባቢ መሆን ይኖርባቸዋል።
  • የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ /CPO/ ወይም የባንክ ጋራንቲ፣ በጥሬ ገንዘብ የተከፈለበት ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ጥቃቅንና አነስተኛ በራሳቸሁ ምርት ብቻ ነው መወዳደር የምትችሉት።
  • ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚዘጋበት ቀንና ስዓት ድረስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ለጠቅላላው ሎት የግዥ ዓይነት የተቀመጠውን የማይመለስ 300.00 /ሦስት መቶ ብር ብቻ/ ለመስሪያ ቤታችን ለፋይናን ዳይሬክቶሬት በመክፈል ሰነዱን ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ሰባተኛ ፎቅ መውሰድ ይቻላል።
  • ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነዶች ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ኤንቨሎፖች/ ፖስታዎች/በማሸግ ኦርጅናል እና ኮፒ የሚል ምልክት /ፅሁፍ/ በማድረግ በተለያየ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባ ይኖርባችኋል።
  • የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ የባንክ ጋራንቲ ወይም ጥሬ ገንዘብ የተከፈለበት ደረሰኝ ኮፒ፣ እንዲሁም ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅት ካቋቋማቸው አካል የተሰጠ የዋስትና ደብዳቤ ኦርጅናል በታሸገ ፖስታ ውስጥ መካተት አለበት። በኦርጅናል እና በቅጅው መካከል ያለመጣጣም ቢከሰት ኦርጅናሉ፤ የበላይነት ይኖረዋል።
  • በመጫረቻ ሰነዱ የቀረበው ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ዕለት ጀምሮ ከ6 ቀናት በላይ የሚወስድ ከሆነ መስሪያ ቤቱ እንደአስፈላጊነቱ ግምገማው እስኪጠናቀቅ ድረስ ተጫራቾች ያቀረቡትን የመጫረቻ ዋጋ እንዲያራዝም የመጠየቅ መብት ያለው ሆኖ ለማራዘም ፈቃደኛ ያልሆነ ድርጅት ከጨረታው ይሰረዛል።
  • ከተገለፀው ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
  • ጨረታው በተጠቀሰው የመክፍቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ የሚከፈት ይሆናል። ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመርኩዞ መጫረት አይችልም።
  • ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /አስር የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ11ኛው ቀን ከጧቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከጧቱ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል
  • ጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻው ቀን በበዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል።
  • የተጫራቾች ተሟልቶ አለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት ስነ ስርዓት አያስተጓጉለውም፡፡
  • ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ላይ ቫትን ያላካተተ ተጫራች የሰጠው ዋጋ ቫትን እንዳካተቱ ተቆጥሮ ይወሰዳል።
  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው። ተጫራቾች የጨረታ ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ7 የቅሬታ መስሚያ ቀናት ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ። እንዲሁም ከ7 የቅሬታው መስሚያ ቀናት በኋላ ባለው 5 የስራ ቀናት ውል መውሰድ ይችላሉ።
  • ተጫራቹ ሰነድ ለመግዛት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000288861815 ላይ በማስገባት የባንክ ደረሰኝ ማምጣት አለባችው በጥሬ ገንዘብ መክፈል አይቻልም

ማስታወሻ፦

1. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ሰነዱ አንድ አካል ተደርጎ ይቆጠራል።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ የሰፈሩትን ዝርዝር መረጃዎች በጨረታ መመሪያው ላይ ሰንጠረዥ የተዘረዘሩትን ግዴታዎች በትኩረት ማንበብ ይኖርባቸዋል።

አድራሻ፦ 22 ለም ሆቴል ዝቅ ብሎ ኤልሳ ቆሎ አጠገብ

በአዲስ አበባ ከተማ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ 01118120087

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ቁ.2


Tender details

  • Deadline: 2026-09-10
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጧቱ 4፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-10 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጧቱ 5፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: አዲስ አበባ ከተማ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Lessan (Aug 29, 2026)
  • Posted at: 2026-08-29T07:42:03.000Z
← Back to all tenders