Plastic Products

የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለሥራ አገልግሎቱ የሚያስፈልጉትን የተለያዩ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ ከብቁና ሕጋዊ ተጫራቾች በማወዳደር ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል

Description

የጨርታ ጥሪ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ግ002/2019 በጀት ዓመት

የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለሥራ አገልግሎቱ የሚያስፈልጉትን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩ የተለያዩ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ ከብቁና ሕጋዊ ተጫራቾች በማወዳደር ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።

ስለሆነም በየዘርፉ የተሰማሩ በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ብቁና ሕጋዊ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ኤጀንሲው ጥሪ ያቀርባል።

ምድብ ቁጥር

አገልግሎት /የዕቃው ዓይነት

 

የጨረታ ሰነድ ዋጋ

የጨረታ ማስከበሪያ

ሎት 1

መንገድ ዳር የሚቀመጥ የደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ የሚውል ደስት ቢን ግዥ

400 ብር

380, 000.00  ብር CPO

ሎት2

ለረጲ (ላንድ ፊል) ውስጥ ለውስጥ መንገድ ስራ የሚውል ገረጋንቲ ድንጋይ ግዥ

400 ብር

210,000.00 ብር CPO

ሎት3

ለረጲ (ላንድ ፊል) ውስጥ ለውስጥ መንገድ ስራ የሚውል ተለቅ ተለቅ ያለ (ቦልድ ድንጋይ ) ግዥ

400 ብር

210,000.00 ብር CPO

ሎት4

ለደረቅ ቆሻሻ መሰብሰቢያ የሚወል በእጅ የሚገፋ ጋሪ

400 ብር

230,000.00 ብር CPO

ሎት5

ደረቅ ቆሻሻ የሚበሰብስ እና የማይበሰብስ የሚለይበት የኤጀንሲው ሎነ እና ህትመት ያለበት ማዳበሪያ /ከረጢት) ግዥ

400 ብር

190,000.00 ብር CPO

ሎት6

ለደረቅ ቆሻሻ መጥረጊያ የሚያገለግል አካፋ ግዥ

400 ብር

100,000.00 ብር CPO

ሎት7

ለደረቅ ቆሻሻ መጥረጊያ የሚያገለግል ዛቢያ/ ጀምባ

400 ብር

180,000.00 ብር CPO

ሎት8

የአደጋ መከላኪያ የተራፊክ ምልክት አንጸባራቂ ኮን

400 ብር

120,000.00 ብር CPO

ሎት9

ግንዛቤ ለመፍጠር ለቅስቀሳ የሚያገለግል መንታርቦ ግዥ

400 ብር

30,000.00 ብር CPO

ሎት10

ለመንገድ ጽዳት ስራ የሚውል መጥረግያ ግዥ

400 ብር

80,000.00 ብር በCPO

ሎት11

ሁነት ዝግጅት

400 ብር

30,000.00 ብር CPO

ሎት12

የኮምፖስት መስሪያ ግብአቶች

400 ብር

40,000.00 ብር CPO

ሎት13

የኮምፖስት ማጣሪያ ወንፊት እና የፒቪሲ ግዥ

400 ብር

50,000.00 ብር CPO

1. ተጨራቾች በጨረታው ለማሳተፍ፡- በዘመኑ የታደሰ እና አግባብነት ያለው የንግድ ሥራ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል የዘመኑ የግብር ከሊራንስ፤ እና በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ መሠረት በሚመለከተው የመንግስት ግዥ አካል ድረ-ገጽ (www.ppa.gov.et ) ላይ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።

2. በሎት 1 የደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ የሚያገለግል ደስትቢን ግዥ ላይ የምትሳተፉ ተጫራቾች፣ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው ዝርዝር መግለጫ (Specification) መሠረት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና (Sample) ማቅረብ ግዴታ ነው።

3. በሎት 2 እና በሎት 3 የተጠቀሱ ግዥዎች የምትሳተፉ ተጫራቾች፣ በሕግ አግባብነት ካለው አካል የተሰጠ የማምረቻ ቦታ ኳሪ እና የባለቤትነት ፈቃድ፣ ለሰብ ቤዝ (የተቆፋሪ ማዕድን) ለማውጣትና ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ሕጋዊ ሰነድ ወይም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የተረጋገጠ የባለቤትነት ማረጋገጫ ውክልና ማቅረብ ግዴታ ነው።

4. ከሎት 4 እስከ ሎት 13 በተጠቀሱት ግዥዎች መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፣ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የምትዋዳደሩበት ዕቃ ዕቃዎች በመስፈርቱ መሰረት ናሙና (Sample) ማቅረብ ግዴታ ነው።

5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በተገለጸው ዋጋ የማይመለስ ክፍያ በጥሬ ገንዘብ በመፈጸም፣ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ 9ኛ ፎቅ መግዛት ይችላሉ።

6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለበት።የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ያለምንም ሁኔታ የሚከፈል (unconditional) መሆን አለበት።

7. አሸናፊ ተጫራች በግዥ አፈጻጸም መመሪያ መሠረት ከጠቅላላ የውል ዋጋ 10% (አሥር በመቶ) የሚሆን የውል ማስከበሪያ ማስያዝ የሚችል።

8. ተጫራቾች ለጨረታው የሚያቀርቡትን የፋይናንሺያል ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን፣ እንዲሁም የቴክኒካል ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻቸው በፖስታ በማሸግ፣ የተጫራቹን ስምና አድራሻ በግልጽ በመጻፍ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችዋል።

9. ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አሥር) የሥራ ቀናት ከቆየ በኋላ፣ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይዘጋል። በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡ 30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የቴክኒካል ሰነዱ በመንግስት ግዥ ዳይሬከቶሬት 10ኛ ፎቅ ይከፈታል። ነገር ግን የጨረታው መከፈቻ ቀን የሕዝብ በዓል ወይም ቅዳሜ እሁድ ከሆነ፣ ሌላ ማስታወቂያ ማውጣት ሳያስፈልግ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ጨረታው ይከፈታል።

10. ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ወይም በሕግ አግባብ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው፣ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 12 75 0002
ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-10
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-10 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Government Cleaning Management Agency
  • Buyer address: ፒያሳ በተለምዶ እሪ በከንቱ ተብሎ በሚጠራው 15 ቀበሌ ኢትዮ ሴራሚክ ጎን (ማእከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ፊት ለፊት የሚገኘው ቢቲ ታወር (ዮናታን ቢቲ ታወር ዮናታን ቢቲ ታወር) የመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት 10ኛ ፎቅ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: በየሎቱ 400 (አራት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 29, 2026)
  • Posted at: 2026-08-29T08:06:58.000Z
← Back to all tenders