Transportation Service

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት በጥሪ ማዕከል የተደገፈ የትራንስፖርት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፡-ኢፕድ 002/2019

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት በጥሪ ማዕከል የተደገፈ የትራንስፖርት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በዉድድሩ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

1. በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ፣በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ታክስ ክሊራንስና በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸዉ፡፡

2. ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ግዥዉን አስመልክቶ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት በመውሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ ከቫት ጋር በመሙላት የጨረታ ሰነዱን ቴክኒክና ፋይናንሽያል በ4 በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናሉንና ኮፒዎቻቸውን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀው በአቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በሚገኘዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

3. ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር 260,000.00(ሁለት መቶ ስልሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/ቢድቦንድ ማስያዝ አለባቸው፡፡

4. ጨረታው ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለዉ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በአቅርቦት መምርያ ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል። ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለዉ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል

5. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- ኢሜይል [email protected] 
አድራሻ ፡አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ፀተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-14
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት
  • Bid opening: 2026-09-14 12:00
  • Bid opening (note): በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሠዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Press Agency
  • Buyer address: አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት
  • Bid bond: 260,000.00(ሁለት መቶ ስልሳ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 100.00 (አንድ መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 30, 2026)
  • Posted at: 2026-08-31T07:38:56.000Z
← Back to all tenders