Cleaning and Janitorial Equipment and Service

ጀብዱ ሞተርስ አክሲዮን ማህበር በ2019 በጀት ዓመት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ መስፈርቱን ከሚያሟሉ ህጋዊ አቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ጀብዱ ሞተርስ አክሲዮን ማህበር በ2019 በጀት ዓመት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ከታች በዝርዝር የተቀመጡትን

  • ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች
  • ሎት 2 የጽዳት መገልገያ እቃዎች
  • ሎት 3 የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች
  • ሎት 4 ብረታ ብረቶች እና የብየዳ እቃዎች /Metals and welding materials/፣
  • ሎት 5 የሰራተኛ ደንብ ልብስ እና የጥንቃቄ እቃዎች፣
  • ሎት 6 የኤሌክትሪክ እቃዎች፣
  • ሎት 7 የተለያዩ ቀለሞች፣
  • ሎት 8 የማሽን መሳሪያዎች (machine shop tools)፣
  • ሎት 9 በፋብሪካ ዉስጥ የመለኪያ መሳሪያዎች/and tools /
  • 9 ሎት 10 ቅባት ና ነዳጅ (lubricant and Gas) ፤
  • ሎት 11 የመኪና መለዋወጫና ሰረርቪስ /Car spare part materials/ በግልጽ ጨረታ መስፈርቱን ከሚያሟሉ ህጋዊ አቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት ጨረታዉን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው። ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ

የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸዉና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ!

2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤

3.የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

4. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 3 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከዋጋ ማቅረብያ ኦሪጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰዉን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው።

ሎት  ቁጥር

የእቃ ዝርዝር

የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ (ETB)

ሎት 1

የጽህፈት መሳሪያዎች ( stationery)

4,000

ሎት 2

የጽዳት መገልገያ እቃዎች (sanitary)

4,000

ሎት 3

የቢሮ ቋሚ እቃዎች / office furniture

7,000

ሎት 4

ብረታብረቶች እና የብየዳ እቃዎች /Metals and welding/

10,000

ሎት 5

የሰራተኛ ደንብ ልብስ እና የጥንቃቄ እቃዎች (uniform Or safety cloth & safety equipment)

3,000

 

ሎት 6

የኤሌክትሪክ ዕቃዎች //

4,000

ሎት 7

ቀለሞች //

3,000

ሎት 8

የማሽን መሳሪያዎች Machine Shop Tool

20,000

ሎት 9

በፋብሪካ ዉስጥ የሚያገለግሉ የእጅ መሳሪያዎች /HAND TOOLS/

3,000

ሎት 10

ቅባት ነዳጅ (lubricant and Gas)

5,000

ሎት 11

የመኪና መለዋወጫና ሰርቪስ /Car spare part materials/

5,000

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይቻላሉ።

7. ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ ኮፒ ማድረግ ኦሪጅናልና ኮፒ ብለዉ በመለየትና በ2 ፖስታ በማሸግ እንዲሁም የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተዉ ኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ ልዩ ቦታ ከተማ አስተዳደር አከባቢ አቡ ሴራ ሁለገብ ሥ/መህበር ህንጻ 4ኛ ፎቅ ላይ ጀብዱ ሞተርስ አ.ማ ጽ/ቤት ዉስጥ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ እስከ 10ኛዉ የስራ ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8. ጨረታዉ በ11ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸዉ በዕለቱ ባይገኙም ጨረታዉ የሚከፈት ይሆናል።

9. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

11. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

አድራሻ - ኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ ልዩ ቦታ ከተማ አስተዳደር አከባቢ አቡ ሴራ ሁለገብ ሥ/መህበር ህንጻ 4ኛ ፎቅ ላይ ጀብዱ ሞተርስ አ.ማ ጽ/ቤት

ለተጨማሪ መረጁ ስልክ ቁጥር 0988850096/0941077274

ጀብዱ ሞተርስ አክሲዮን ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-09-10
  • Bid closing time: 16:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10ኛዉ የስራ ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-11 10:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Jebdu Motors S.C.
  • Buyer address: ኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ ልዩ ቦታ ሰንሻን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 30, 2026)
  • Posted at: 2026-08-31T08:41:01.000Z
← Back to all tenders