Building Construction

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኸምራ ዞን የሠቆጣ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን እና ግንባታ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል

Description

ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኸምራ ዞን የሠቆጣ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለወረዳው በ2018 ዒ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጸውን ከተራ ቁጥር 1 እስከ ተራ ቁጥር 9 ድረስ ያሉ ግንባታዎች ና አቅርቦቶች በሎት/ ጠቅላላ ድምር ከተራ ቁጥር 10 እስከ ተራ ቁጥር 12 ድረስ ያሉ በነጠላ ዋጋ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ፡ -

  • 1. ባለ 4 ወለል ህንጻ ግንባታ ህንፃ ተቋራጭ /BC/ ከሆነ ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ ያስው መሳተፍ ይቾሳስ በጠቅላላ ስራ ተቋራጭ/GC/ ከሆነ ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ያለው መሳተፍ ይችላል።
  • 2. ህትመት
  • 3.ጽ/መሳሪያ
  • 4. ደንብ ልብስ
  • 5. የጽዳት እቃ
  • 6 የመኪና ዕቃ መለዋወጫ
  • 7. የመኪና ጎማ
  • 8. የስፖርት ትጥቅ
  • 9. የተሽከርካሪ ዘይትና ቅባት
  • 10. ፈርኒቸር
  • 11. ኤሌክትሮኒክስ
  • 12. የህንጻ መሳሪያ

ስለዚህ የሚከተሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾቾ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

1. ተጫራቾች በዘርፉ የ2019 ዓ.ም ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3. የግዥ መጠናቸው ከብር 200000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማረ እሴት ታከስ VAT/ከፋይ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4. በፌዴራል ደረጃ ካላቸው የምስክር ወረቀት በተጨማሪ በክልሉ ኮንስትራከሽን ባለስልጣን የአጭር ጊዜ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው መሆን አለበት፡፡

5. ተጫራቾች ጨረታ በመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::

6. የግንባታውም ሆነ የአቅርቦቱ አይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1 ለተገለጸው የህንጻ ግንባታ ለአንዱ ሰነድ የማይመለሰ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር ከተራ ቁጥር 2 እስከ ተራ ቁጥር 12 ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 50/ሃምሳ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከገንዘብ ቤት መግዛት ይችላሉ።

8. የግንባታው ጨረታ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ21 /ሃያ አንድ )ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል:: የእቃ ግዥ ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል።

9 ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሚወዳደሩበት የግንባታ ጠቅላላ ዋጋ 1% ለእቃ አቅርቦት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ | CPO / ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በሰቆጣ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በመ/ሂ-3 ገቢ አድርጎ ኮፒውን ከዋናው የጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

10. ማንኛውም ተጫራቾች የዕቃ ግዥ የጨረታ ሀሳቡን በአንድ በታሽገ ፖስታ እና የህንጻ ግንባታ ስራ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል መረጃዎችን በተለያየ ፖስታ በማሽግ በግዥ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት የእቃ ግዥ ከ 24/12/2018 እስከ 3/1/2019 ዓ.ም ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን፡፡ በተጨማሪም በጨረታ ሰነዱ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፣ ሙሉ አድራሻ፣ የድርጅቱ ማህተም መሟላት ያለባቸው ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4/1/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጉ በ4፡00 ስዓት ግዥ ን/ስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል። የቢሮ ግንባታና ጨረታ ከ 24/12/18 እስከ 8/1/2019 ዓ.ም ጨረታው አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን። በተጨማሪም በጨረታ ሰነዱ ላይ ስማቸው፣ ፊርማቸውን፣ ሙሉ አድራሻ፣ የድርጅቱ ማህተም መሟላት ያለባቸው ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን 9/1/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ግዥ ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል፡፡

11. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀን ውስጥ የዋጋውን 10% በባንከ በተረጋገጠ /CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ መሂ- በማስያዝ ውል መፈረም ለለባቸው፡፡

12. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ አስይዘው ውል ካልፈረሙ መ/ቤቱ የጨረታ ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው::

13. መ/ቤቱ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 ለቀረቡት የጨረታ ሰነድ ማንኛውም ህጋዊ ተወዳዳሪ የሚወዳደርባቸውን የጨረታ ሰነዶች በጨረታ ሰነዱ ላይ የቀረቡት የግንባታ አይነትና የግዥ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን/ መሰረት የመሙላት ግዴታ አለበት፡፡

14. አሸናፊው የአሸነፈውን ግንባታ ከሚፈለግበት ቦታ ሰርቶ የማስረከብና ግዥውን በሚፈለግበት ሴክተር መ ቤት በማስረከብ ሂሳቡን በስሙ የማወራረድ ግዴታ አለበት።

15. በጨረታው ቅሬታ ያላቸው ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተና አሸናፊው ከተለየ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ባለው ቅሬታቸውን ለሚመለከታቸው አካል ማቀረብ አለባቸው። ከተጠቀሰው ቀን በኋላ የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት የለውም::

16. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0334400416 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

18, ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::

19. የጨረታው መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም::

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኸምራ ዞን የሠቆጣ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-19
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-09-19 12:00
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Sekota Woreda FEDB
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published on: Addis Zemen (Aug 30, 2026)
  • Posted at: 2026-08-31T08:47:56.000Z
← Back to all tenders