Spare Parts and Car Decoration Materials
የምስራቅ ሐረርጌ የፈዲስ ግብርና ምርምር ማዕከል ለ2019 የመኪና መለዋወጫ፣ የፅህፈት መሳሪያ፣ ቋሚ እቃዎች፣ የጽዳት እቀዎች፣ የመኪና ጎማዎች፣ ኤሌክትሮኒክሶች እና ጥሬ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የፈዲስ ግብርና ምርምር ማዕከል ለ2019 የመኪና መለዋወጫ፣ የፅህፈት መሳሪያ ቋሚ እቃዎች ፣ የጽዳት እቃዎች ፣ የመኪና ጎማዎች ፤ ኤሌክትሮኒክሶች እና ጥሬ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤
ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
1. በሚወዳደሩበት ዘርፍ የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና የተሟላ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ግብይቱ ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ )ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
3. ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የንግድ ምዝገባ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው ።
4. ተጫራቾች በሚያቀርቡበት ሃሳብ መስጫ ስማቸውን ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች የመወዳዳሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም ።
6. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ ሆኖ ለወደፊት በመንግስት ለሚያወጣ ጨረታ እዳይሳተፉ ሊደረግ ይችላል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500 ብር ብቻ በመክፈል ከፈዲስ ግብርና ምርምር ማዕከል መግዛት ይችላሉ ።
8. የሚገዙትን ማቴሪያሎች ዝርዝር መግለጫ ከሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን ብቻ ለብቻ ከሁሉም የንግድ ማስረጃዎቻቸው ጋር በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።
10. ተጫራቾች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ለ15 የስራ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን 4፡00 ላይ ተዘግቶ 4፡30 ላይ ይከፈታል።
11. 20,000 (ሃያ ሺ ብር) የባንክ ጋራንቲ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችል።
12. የጨረታ ማስተባበያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የመጣ የጨረታ ሰነድ ከጨረታ ሳጥን ውስጥ ሳይገባ ተመላሽ ይሆናል።
13. መስሪያ ቤቱ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. ከ ሐረር store/ስቶር/ ያላቸው።
ማሳሰቢያ > መስሪያ ቤቱ ግዢውን በነጠላ ዋጋ ወይም በሎት ሊያወዳድር ይችላል። ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ 0256667549/0256667550 መጠየቅ ይችላሉ አድራሻ፡- ከሐረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 500ሜ ገባ ብሎ
የምስራቅ ሐረርጌ የፈዲስ ግብርና ምርምር ማዕከል
Tender details
- Deadline: 2026-09-17
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ለ15 የስራ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን 4፡00
- Bid opening: 2026-09-17 12:00
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ለ15 የስራ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን 4፡30
- Region: Oromia
- Publishing entity: Fedise Agriculture Research Center
- Bid bond: 20,000 (ሀያ ሺህ ብር)
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 30, 2026)
- Posted at: 2026-08-31T08:55:49.000Z