Vehicle
የጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ብዛት አንድ ባለ 12ቶን ከሬን ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈጸም ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ብዛት አንድ ባለ 12ቶን ከሬን ተሸከርካሪ በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መረጃዎች በማቅረብ በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡-
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
- የግብር ከፋይነት ሰርቲፊኬት (TIN) ያላቸው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ /VAT Register / የሆኑና
- የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ የጠቅላላ ዋጋውን 1% በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (C P O) ወይም ህጋዊ በጊዜ ያልተገደበ የባንክ ዋስትና ማስያዝ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ ቁጥር 27 ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ድረስ መግዛት ይችላሉ፤
- በጨረታ ዝርዝሩ መሰረት ዋጋቸውን በመሙላትና በፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ድረስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ን/የስራ ሂደት ቢሮ (ቢሮ ቁጥር 14) ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የተወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ተለያይቶ በታሸገ ኢንቨሎፕ አንድ ኦርጅናል ቴክኒካልና ፋይናንሻል እና አንድ ኮፒ ቴክኒካልና ፋይናንሻል የያዙ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ታሽጎ ከጧት 4፡30 ለመገኘት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- በአገር አቀፍ በዓላት ካልተዘጋ በስተቀር ዘወትር ቅዳሜ እስከ 6፡00 ሰዓት የስራ ቀን ሲሆን ይህም እንደ አንድ የስራ ቀን ይቆጠራል፡፡
- ድርጅቱቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 211 3316/0581120697 በመደወል ማነጋገር ይችላሱ፡፡
በጎንደር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ፤
ግዥና ንብረት አስተዳደር
Tender details
- Deadline: 2026-09-14
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-14 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጧቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Gonder City Water and Sewerage Service Bureau
- Bid bond: ለእያንዳንዱ 1%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 30, 2026)
- Posted at: 2026-08-31T09:17:14.000Z