Textile, Garments and Uniforms
አበበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት አመት የተለያየ በሎት ምድብ የተከፋፈለ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Textile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather Products
Addis Ababa
More tags
StationeryOffice Supplies and ServicesMaterialsEducation and TrainingCleaning and Janitorial Equipment and ServiceEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesPrinted Advertising MaterialsAdvertising and PromotionPrinting and PublishingPharmaceutical ProductsHealth Care, Medical IndustryOffice FurnitureFurniture and FurnishingBuilding and Finishing MaterialsConstruction and Water WorksHealth Related Services and MaterialsMedical Equipment and SuppliesAmharic2merkatoAbebech Gobena Primary School
Description
የ1ኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግል መለያ ቁጥር አበበች ጎበና /አጸ/ ህጻ /የመ/ደ/ት/ቤት 01/2019 ዓ.ም አበበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት አመት የተለያየ በሎት ምድብ የተከፋፈለ እቃዎችን ማለትም
- ሎት1 የደንብ ልብስ (የስራ ልብስ)
- ሎት2 የደንብ ልብስ ስፌት
- ሎት 3 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- ሎት4 (አላቂ የትምርት ዕቃዎች)
- ሎት 5(አላቂ የጽዳት ዕቃዎች )
- ሎት 6 ( ዝቅተኛ ቋሚ ዕቃዎች)
- ሎት 7(ቋሚ ፕላንትና ማሽነሪ)
- ሎት 8(ቋሚ ህንጻ ቁሳቁስ)
- ሎት 9(የህትመት ስራዎችን)
- ሎት 10 አላቂ የህክምና እቃዎች
በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡
- በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉ መሆነቸውንና በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚቸሉ፤
- በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ የንግድ ምዝገባ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና አቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በመንግስት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ከላይ የተጠቀሱትን እቃዎች ዝርዝር የሚያሳውቅ የግዥ የግልጽ ጨረታን የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400/አራት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት አበበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ግዥ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 1 ማግኘት ይቸላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማሰረከቢያ የሚያገለግል የሚወዳደሩበትን 2% ፐርሰንት በት/ቤቱ ስም በተዘጋጀው ሲፒኦ ከኦርጅናል ማስረጃ ፖስታ ውስጥ ሲፒኦ በማድረግ በመያዝ ማረጋገጫውን ከሚወዳደሩበት ሰነዶቻቸው ጋር ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ እንዲሁም ጨረታውን ካሸነፉ ደግሞ ወዲያውኑ የውል ማስከበሪያ የሚሆን ያሸነፉበት የገንዘብ መጠን 10% ሲፒኦ በማሰራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ለውል ማስከበሪያ አያገልግልም፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን መስሪያ ቤቱ ባቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር ላይ የአንዱ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላት የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለ ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰአት በአበበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ ለዚሁ ጨረታ ሰነድ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድና ለመወዳደር የሚያስፈልጉ ዝርዝር ሰነዶች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለሁሌም እቃዎች የቅርብ ጊዜ ምርት (ጊዜው ያላለፈበት ምርት) ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ለአንድ እቃ አንድ ናሙና መቅረብ አለበት ፡፡
- ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ማህተም በማድረግ በታሸገ ካኪ ፖስታ ሳጥን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የህትመት ስራዎችን ት/ቤቱ ባዘጋጀው ናሙና መሰረት ሰርተው ማቅረብ አለባቸው::
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከ11ኛ የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሸጎ በእለቱ 4:30 ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም አበበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ይከፈታል፡፡
- ጥቃቅንና አነስተኛ እራሳቸው አምራችና የአገር ውስጥ ምርት የሚያቀርቡ ከሆኑ ልዩ አስተያየት ይደረግላቸዋል፡፡
- በተጨማሪም ወደኛ ሰነድ ለመውሰድ ስትመጡ አምራች ስለመሆናችሁና የአገር ውስጥ ምርት መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ አለባችሁ፡፡ ነገር ግን አምራችና የአገር ውስጥ ምርት አቅራቢ ካልሆናችሁ እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ መግዛትና ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባችኋል፡፡ በተጨማሪ መወዳደር የሚችሉት በተደራጁበት ዘርፍ ላይ ብቻ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ት/ቤቱ ባዘጋጀው ሰነድ ነው ሞልቶ ማቅረብ የሚቻለው ከዚያ ውጪ ለሚያመጣ ውድቅ ይደረጋል፤ በተጨማሪም ማንኛውም ተጫራች ሰነዱን ሙሉ ለሙሉ መግዛት ይኖርባችኋል::
- ተጫራች ያሸነፉባቸውን ግብዓቶች (እቃዎች) በራሳቸው ትራንስፖርት በት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ንብረት ክፍል ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል::
- ት/ቤቱ የተሻለ የግዢ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ አድራሻችን-ዮሐንስ ጸበል አካበቢ ወደ አቤት ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ
ወደ ውስጥ በሚያስገባው ወይም በተለምዶ አይሻ መስጊድ አጠገብ
ስልክ ቁጥር 0118126317/ 0919492536/ 0902373975
አበበች ጎበና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-12
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከ11ኛ የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-12 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከ11ኛ የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Abebech Gobena Primary School
- Buyer address: ዮሐንስ ጸበል አካበቢ ወደ አቤት ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ወደ ውስጥ በሚያስገባው
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 30, 2026)
- Posted at: 2026-08-31T09:56:23.000Z