Chemicals and Reagents

ፌዴ/ማረ /ቤት/ ኮሚሽን ጠ/ሆስፒታል ልዩ ልዩ መድሃኒቶች እና የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች፣ የምግብ ግብዓቶች፣ የጥገና ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የፅህፈት መሳሪያዎች እና የህትመት ውጤቶች በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር ፌዴ/ማረ /ቤት/ ኮሚሽን ጠ/ሆስፒታል – 009/2019 ዓ.ም በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2019 በጀት ዓመት ከዚህ ቀጥሎ በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  1. ሎት አንድ (01) ልዩ ልዩ መድሃኒቶች እና የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች
  2. ሎት ሁለት (02) የምግብ ግብዓቶች፣
  3. ሎት ሶስት (03) የጥገና ዕቃዎች፣
  4. ሎት አራት (04) የደንብ ልብስ፣
  5. ሎት አምስት(05) የፅዳት ዕቃዎች፣
  6. ሎት ስድስት (06) የፅህፈት መሳሪያዎች፣
  7. ሎት ሰባት (07) የህትመት ውጤቶች፣

በዚህ መሠረት፡-በግልፅ ጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን ሠነዶች /ማስረጃዎች/ ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. በሚወዳደሩበት ዘርፍ የተፈቀደላቸው የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፤
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣
  3. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
  4. ከሎት አንድ /01/ ውጪ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣
  5. በሚወዳደሩበት ዘርፍ በ ግዥ ኤጀንሲ ድረ-ገፅ www.ppa.gov.et በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
  6. ጊዜው ያላለፈ ከሀገር ውስጥ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን የተፃፈ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፣
  7. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለእያንዳንዱ እቃ ከሎት አንድ /01/ ውጭ ናሙና ሳንፕል ለሚያስፈልጋቸው ናሙና በአግባቡ መዝገበው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  8. መድሃኒትና የላብራቶሪ ሪኤጀንት ከሆነ ከምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የታደሰ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ከ16/አስራ ስድስተኛው ቀን ጀምሮ የሚከፈት እና የሚዘጋ ሲሆን የእያንዳዱ ሎት የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀን በእያንዳዱ ሎት ሰነድ ላይ የሚጠቀስ ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ዝርዝር ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት ብር 2000/ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል በፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ጠቅላላ ሆስፒታል በተከፈተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ባንክ ሣጥን ቁጥር 1000007971568 ገቢ በማድረግ ህጋዊ የባንክ ደረሰኝ እያቀረቡ የጨረታውን ሰነድ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1/አንድ/ 100,000/አንድ መቶ ሺህ/ ብር ለሌሎች ሎቶች ማለትም ለ2፣3፣4፣5፣6 እና 7 ደግሞ 20,000 /ሃያ ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒዮ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ  የተጠበቀ ነው

አድራሻ ፡- አዲስ አበባ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ሸገር ዳቦ ቤት ጎን የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ጠቅላላ ሆስፒታል።

ለተጨማሪ መረጃዎች በስልክ ቁጥር 0947232233 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

ፌዴ/ማረ/ ቤት /ኮሚሽን ጠ/ሆስፒታል


Tender details

  • Deadline: 2026-09-17
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ከ16/አስራ ስድስተኛው ቀን
  • Bid opening: 2026-09-17 17:00
  • Bid opening (note): በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ከ16/አስራ ስድስተኛው ቀን
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Prison Commission General Hospital
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: ብር 2000/ሁለት መቶ/ ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Aug 30, 2026)
  • Posted at: 2026-08-31T10:11:21.000Z
← Back to all tenders