Shoes and Other Leather Products

ብርሃን ባንክ አ.ማ. በ2019 በጀት ዓመት ለሰራተኛች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የጫማ ግዥ ለማከናወን በዘርፉ የተሰማሩ ፋብሪካዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

አገር አቀፍ የግልጽ ጨረታ

የጨረታ ቁጥር ብ/ባ/ግጨ/ጫማ/2026/27/15

1. ብርሃን ባንክ አ.ማ በ2019 በጀት ዓመት ለሰራተኛች አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተዘረዘሩትን የተለያዩ የጫማ ግዥ ለማከናወን በዘርፉ የተሰማሩ ፋብሪካዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

.

የጫማ አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ መጠን

1

የወንዶች ጉርድ ቆዳ ጫማ ደረጃውን በጠበቀ በሁለት አይነት ቀለም

100,000.00

2

የሴቶች ቆዳ ጫማ ደረጃውን በጠበቀ በሁለት አይነት ቀለም

30,000.00

2. ተጫራቶች ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ የምስክር ወረቀት እና የታክስን ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::

3. ተጫራቶች የማይመለስ ብር 345.00 (ብር ሦስት መቶ አርባ አምስት) በማንኛውም የብርሃን ባንክ አ.ማ ቅርንጫፍ ክፍያ ፈጽመው ደረሰኙን በማቅረብ ከባንኩ ዋና መ/ቤት ከሚገኝበት ቦሌ ድልድይ ወመሳድኮ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ከሰፕላይ ቼን እና ውል አስተዳደር መምሪያ ቢሮ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ::

4. ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን ህጋዊ ሰነዶችና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሰነድ በአንድ ፖስታ እና የዋጋ ሰነድ በሁለተኛ ፖስታ በዋና እና በኮፒ ማቅረብ ሲኖርባቸው ለሚሳተፉበት ጫማ ናሙና ማቅረብ ግዴታ አለባቸው::

5. ተጫራቶች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ በባንኩ ዋና መ/ቤት በሚገኝው ቦሌ ድልድይ ወመሳኮድ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ከሰፕላይ ቼን እና ውል አስተዳደር መምሪያ ቢሮ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::

6. ጨረታው መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተገለጸው ቢሮ ይከፈታል::

7. ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኝ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው::

ብርሃን ባንክ አ.ማ.

ከሰፕላይ ቼን እና ውል አስተዳደር መምሪያ

ስልክ ቁጥር 0116 632 097 / 0116 507 422


Tender details

  • Deadline: 2026-09-15
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-15 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Berhan Bank S.C.
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 345.00 ብር
  • Published on: Reporter (Aug 30, 2026)
  • Posted at: 2026-08-31T12:46:05.000Z
← Back to all tenders