Printing and Publishing

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን ተጫራቾችን በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ህ/ተ/በጎ/ፈ/ማ/ኮ ህ01/2019

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ በሎት የተጠቀሱትን ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን ተጫራቾችን በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም

የጨረታ አይነት በሎት

የጨረታ ማስከበሪያ ..

ሎት 1. የህትመት አገልግሎት

40,000.00 ብር

ሎት2. የኩነትና የመድረክ አገልግሎት

40,000.00 ብር

ሎት3. የአላቂ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ-

25,000.00 ብር

ሎት4. የኤሌክትሪክ የሚኒባስ ተሽከርካሪ ኪራይ

50,000.00 ብር

ሎት5. የጋራዥ አገልግሎት ግዥ-

50,000.00 ብር

ሎት 6 የክህሎትና የባህሪ/ማይንድ ሴት/ ስልጠና አገልግሎት ግዥ

15,000.00 ብር

ሎት 7. የቋሚ ዕቃዎች ግዥ

50,000.00 ብር

ሎት 8. የሚዲያ አገልግሎት ግዥ

30,000.00 ብር

1. ተጫራቾች በጨረታ መሳተፍ የሚችሉት በዘርፋ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ንግድ ምዝገባ፣ ግብር ከፋይ ሰርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት እና የአቅራቢነት ተመዝጋቢ መረጃ ማቅረብ የሚችል፣ እንዲሁም ሌሎች እንደ አስፈላጊነቱ ለጨረታ ግምገማ የሚውሉ መረጃዎች በማቅረብ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

2. ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10/አስር/የስራ ቀናት ውስጥ በግዥ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀውን ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ሰነድ በማይመለስ የአንዱን ሰነድ በ400/ አራት መቶ ብር/ ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10/አስር/ የስራ ቀናት ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት እስከ ማታ 11፡30 ሰዓት ድረስ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ የቴክኒካልና የፋይናንሻል ሰነዶቻቸውን ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በአንድ ፖስታ ከተጓዳኝ ማስረጃዎች ጋር ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት አስቀድሞ በ11ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰአት ድረስ በማስገባት የሚታሸግ ሲሆን ጨረታው በዚሁ ዕለት 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ማግስቱ የበአል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው ቀን በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡

4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ሲመልሱ ናሙና ለተጠየቀባቸው ማምጣት ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ናሙና ማቅረብ ለማይቻልባቸው ዕቃዎች ገላጭ ፎቶ ተያይዞ እንዲቀርብ እያሳወቅን ተጫራቹ የመጫረቻ ሰነዳችሁን ስትመልሱ ተቋማችን ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድና በጨረታው በተቀመጠው ዝርዝር መግለጫ መሠረት ብቻ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡ ከዚህ ውጪ በራሱ ሰነድ የሚያቀርብ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡

5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመሸጫ ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ45 ቀናት የፀና ይሆናል፡፡

6. ተቋማችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

7. ተጫራቹ ለጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ሲያሰራ ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት 45 ቀናት በተጨማሪ የ5 ቀናት ተጨምሮበት ተሰርቶ መቅረብ አለበት፡፡ በድምሩ የ60 ቀናት

8. አድራሻ፡- ፒያሳ እሪበከንቱ ቢቲ ታወር 3ኛ ፎቅ ይገኛል፡፡

9. ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- +251111124738

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና
በጎፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-09-12
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰአት
  • Bid opening: 2026-09-12 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን እስከ 4፡30 ሰአት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Administration Community Participation and Coordination Commission
  • Buyer address: ፒያሳ እሪ በከንቱ ቢቲ ታወር 3ኛ ፎቅ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: የአንዱን ሰነድ 400 (አራት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 31, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T07:52:25.000Z
← Back to all tenders