Catering and Cafeteria Services

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ለሁለት ዓመት የሚቆይ የሠራተኞች መዝናኛ ክበብ የግብአት አቅርቦትና የመስተንግዶ አገልግሎት፣ ደንብ ልብስ (የሥራ ልብስ) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 023/18

ድርጅታችን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በጨረታ አንድ (ሎት 1)፦ ለሁለት ዓመት የሚቆይ የሠራተኞች መዝናኛ ክበብ የግብአት አቅርቦትና የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ፤

በጨረታ ሁለት (ሎት 2)፦ ለሁለት ዓመት በሚቆይ ውል ለሠራተኞች የሚሆን የደንብ ልብስ (የሥራ ልብስ) ማለትም፦ ሙሉ ቱታ ብዛት 721፣ ጋዋን ብዛት 660፣ ሸሚዝ ብዛት 186፣ ሙሉ ልብስ (ብትን ጨርቅ) ብዛት 520 ሜትር፣ ከረባት ብዛት 186፣ የቆዳ የእጅ ጓንት ብዛት 150፣ የፕላስቲክ የእጅ ጓንት ብዛት 300 እና የሹራብ የእጅ ጓንት ብዛት 150 ግዥ፣ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት (አራት ኪሎ) አዲስ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 300.00 ከፍለው በመግዛት የፋይናንሺያል እና የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ሕንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው።

ጨረታው 21/1/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶከመንቶች፣ የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ሕንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል። የፋይናንሽያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው።

ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።

ስልክ ቁጥር 011-155-5230

ድረ ገፅ (www.ethbspe.org)

Berhanena selam printing enterprise

አዲስ አበባ

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-01
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-10-01 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Berhanena Selam Printing Enterprise
  • Buyer address: Addis Ababa, Ethiopia
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 31, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T08:49:29.000Z
← Back to all tenders