Textile, Garments and Uniforms

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት ለወረዳው የሚያስፈልገውን የተለያዩ ግብዓት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት ለወረዳው የሚያስፈልገውን የተለያዩ ግብዓት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

ስለዚህ በዚህ ስራ ላይ የተሰማራችሁ ነጋዴዎች፤አቅራቢዎች፤ አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች ሕጋዊ ውክልና ያላችሁ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉት ቀርባችሁ መወዳደር እንደምትችሉ እንገልፃለን ::

በዚህም መሰረት

  • ሎት-1 የደንብ ልብስ ግዥ-የጨረታ ማስከበሪያ ብር 59,478.48
  • ሎት-2 የፅህፈት መሳሪያ ግዥ-የጨረታ ማስከበሪያ ብር 22,723.18
  • ሎት-3 የፅዳት ዕቃዎች ግዥ-የጨረታ ማስከበሪያ ብር 59,781.97
  • ሎት-4 የህትመት አገልግሎት ግዥ-የጨረታ ማስከበሪያ ብር 8,235
  • ሎት-5 የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች ግዥ-የጨረታ ማስከበሪያ ብር 19,381.46
  • ሎት 6 የጭነት አገልግሎት ግዥ-የጨረታ ማስከበሪያ ብር 13,851.1
  • ሎት-7 ልዩ ልዩ ኪራይ ዕቃዎች አገልግሎት ግዥ-የጨረታ ማስከበሪያብር 8000
  • ሎት-8 የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች ጥገና አገልግሎት ግዥ-የጨረታ ማስከበሪያ ብር 8000

የጨረታው መስፈርት

1.ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት በዘርፉ ያለው፤

2.የመንግስት ግብር የከፈለ ክሊራንስ ያለው

3. VAT ተመዝጋቢ የሆነ፤

4. በመንግስት ግዥዎች በአቅራብነት የተመዘገበበትን ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤

5. የተፈለገውን የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ በአንድ ጊዜ ማቅረብ የሚችል፤

6. በተባለበት ቦታና ቀን እቃውን ቢሮ ድረስ ማቅረብ የሚችል፤

7. በስራ ከሎት የተደራጁት ኢንተርፕራዝ በተደራጁበት የስራ ዘርፍ አምራች ከሆነ አምራችነቱን የሚገልጽ፤ አገልግሎት ዘርፍ ከሆነ የሚሰጡት አገልግሎት እና ንግድ ዘርፍ ከሆነ ከሀገር ውስጥ አምራች ጋር የተዋዋሉበት ውል መረጃ በማቅረብ ብቻ ልዩ ድጋፍ የሚደረግላቸው ሲሆን ይህም የሚደረገው ከአደራጀቸው ጽ/ቤት ኃላፊ በተፈረመ የድጋፍ ዳብዳቤ ይሆናል። ከአገር ውስጥ ምርት ዉጭ ለሆኑት እንደማንኛዉም ነጋዴ የሚስተናገዱ ይሆናል።

8 የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር ብቻ) ከፍሎ መግዛት የሚችል፤

9.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ የሚጫረቱበትን ለእያንዳንዱ ሎት 1 ሎት 10 የገንዘብ ተተምኖ በተቀመጠው መሰረት ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበርያ ያላስያዘ በጨረታው ሰነድ የመጀመርያ ምርመራ ውድቅ ይሆናል።

10.የጨረታ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ እስከ መ/ቤቱ ግምጃ ቤት/ ንብረት ክፍል/ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

11.የጨረታ ሰነድ ኮፒና ኦርጅናሉን ተቋሙ ባዘጋጀው በታሸገ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።

12.የጨረታ ማስገቢያ ቦታ ለአቃቂ ቃሊቲ/ክ/ከ/ወ/3/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 11 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ::

13.ተጫራቾች ከጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው ።

14.ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለዉጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታዉ እራሳቸዉ ማግለል አይቻልም።

15.አሸናፊው ተጫራች የዉል ማስከበሪያ የጠቅላላ ግዥዉን 10% በብር ሕጋዊ CPO/ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

16. የጨረታ ሰነድ ጨረታዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት ብቻ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቱሉዲምቱ አለም ባንክ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ፊትለፊት አጂካ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 11 ሰነድ መግዛት ይቻላል፡፡

17. ጨረታዉ በአስራ አንደኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተጫራቹ ህጋዊ ወክል በተገኘበት ታሽጎ በ4፡30 የሚከፈት ሲሆን ተጫራቹ ህጋዊ ወክሉ| ያለመገኘት የጨረታ አከፋፈት ላይ ተጽኖ አያመጣም። አስራ አንደኛዉ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣይ ስራ ቀን የሚከፈት መሆኑን እናሳዉቃለን።

18. ዉድድሩን ያሸነፈ ተወዳዳሪ ዉድድሩን ማሸነፉ ከታወቀ እና 7 የቅሬታ ቀን ከአለቀ በኃላ በ5 (አምስት) የስራ ቀን ዉስጥ በአካል ቀርቦ የዉል ስምምነት መፈረም አለበት ።

19. ለደንብ ልብስ፣ለፅህፈት መሳሪያ እና ለፅዳት ዕቃ ተወዳዳሪዎች ምንም አይነት መለያ ምልክት ያልተደረገበት ለእያንዳንዱ እቃ አንድ ናሙና ብቻ አቃቂ ቃሊቲ ከፊለ ከተማ ወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

20. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ዉድድሩን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ይሆናል።

21, ለበለጠ መረጃ ከፈለጉ 0912 807 618 ወይም 0912 067 342

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-14
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00
  • Bid opening: 2026-09-14 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Akaki Kality Sub City Woreda 13 Administration Finance Office
  • Buyer address: አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 አስተዳደር አጂካ ኢትዮጵያ ህንጻ አርሴማ አደባባይ ዝቅ ብሎ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 400 (አራት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 31, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T09:14:39.000Z
← Back to all tenders