Materials

በቦሌ ክ/ከተማ ት/መምሪያ የቦሌ ህብረተሰብ ሁለተኛ ደ/ት/ቤት በ2019 ዓ/ም ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 0001/2019 ዓ/ም

በቦሌ ክ/ከተማ ት/መምሪያ የቦሌ ህብረተሰብ ሁለተኛ ደ/ት/ቤት በ2019 ዓ/ም ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል

  • ሎት 1. አላቂ የት/ዕቃዎች እና የተለያዩ የፅ/መሳሪያዎች፣
  • ሎት 2. አላቂ የፅዳት ዕቃዎች ፣
  • ሎት 3. ቋሚ ዕቃዎች፣
  • ሎት 4. የስፖርት ዕቃዎች፣
  • ሎት 5. የጥገና ዕቃዎች፣
  • ሎት 6. የደንብ ልብስ፣
  • ሎት 7.ደንብ ልብስ ስፌት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

1. ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና በመንግሥት የአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።::

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለባቸው።

3. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ለእያንዳንዱ በሎት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከት/ቤቱ ፋይናንስ ቁጥር 5 /አምስት/ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ የሚሆን ብር ሎት 1 አላቂ የት/ዕቃዎች እና የተለያዩ የፅ/መሳሪያዎች 4000.00 /አራት ሺህ ብር/ ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች 4000.00 /አራት ሺህ ብር/ ሎት 3 ቋሚ ዕቃዎች 10,000.00/ አስር ሺህ ብር/ ሎት 4 የስፖርት ዕቃዎች 5,000.00/አምስት ሺህ ብር/ ሎት 5 የጥገና ዕቃዎች 4,000.00 /አራት ሺህ ብር/ ሎት 6 የደንብ ልብስ 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ ሎት 7 ደንብ ልብስ ስፌት 2,000.00 /ሁለት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ ፒ ኦ በቦሌ ህብረተሰብ ሁለተኛ ደ/ት/ቤት ስም አሠርተው ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ጨምረው በመሙላት የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናል ና ኮፒ በተለያዩ ፖስታ ውስጥ በማድረግ በታሸገና ማህተም ባረፈበት ኤንቭሎፕ በማድረግ በት/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፣ በአስረኛው ቀን በ11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በአሰራ አንደኛው የስራ ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያውና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

7. ተጫራቾች ከጨረታ መክፈቻ ቀን በፊት የሚወዳደሩበትን ዕቃ ናሙና ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በቴክኒክ ፍላጎት የሚገመገም ይሆናል።

8. አሸናፊ ተጫራቾች ውል በሚዋዋሉበት ወቅት ላሸነፉበት ዕቃ የሚውል የውል ማስከበሪያ 10% CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

9. ት/ቤቱ በዕቃዎች ላይ 20% የመጨመር እና የመቀነስ መብት አለው።

10.ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የሚገኝ ሲሆን ልዩ ቦታ ቦሌ ሆምስ ስልክ ቁጥር፡ 0118222511

በቦሌ ክ/ከተማ ት/መምሪያ የቦሌ ህብረተሰብ ሁለተኛ ደ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-10
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን በ11፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-12 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው የስራ ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bole Community Primary and Secondary School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Aug 31, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T09:25:58.000Z
← Back to all tenders