Chemicals and Reagents
በልደታ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኘው ወረዳ 04 ጤና ጣቢያ የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ የህክምና ዕቃዎችና ሪኤጀንቶች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ጥገና፣ የፅህፈት ዕቃዎች፣ ደንብ ልብስ እና የህትመት ስራዎች መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ 1ኛ
በልደታ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኘው ወረዳ 04 ጤና ጣቢያ የሚከተሉትን እቃዎች መግዛት ይፈልጋል የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ የህክምና ዕቃዎችና ሪኤጀንቶች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ጥገና፣ የፅህፈት ዕቃዎች፣ ደንብ ልብስ፣ የህትመት ስራዎች ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር /Suppliers list መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ከመንግስት ግዥ ኤጀንሲ የተሰጠ የምስክር ወረቀት እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 120 /አንድ መቶ ሃያ ብር በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ግዢ ክፍል በአካል ቀርቦ መግዛት ይቻላል።
3. የጨረታ ማስከበሪያ ለህክምና ዕቃ ብር 20,000/ሀያ ሺህ ብር/ እና ሪኤጀንት ብር 20,000 /ሀያ ሺህ ብር/ ፈርኒቸር ዕቃ 20,000/ሀያ ሺህ ብር ለጥገና 20,000 (ሀያ ሺህ ብር) ለኤሌክትሮኒክስ 20,000(ሀያ ሺህ ብር ) እና ለሌሎች ለያንዳንዳቸው ሎት 5000 ብር /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ ዝርዝር ዋጋና መለያ ቁጥር በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማህተም ና ፊርማ በማኖር በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ (የተሞላ ሙሉ ሰነድ) 4ኛ ፎቅ ግ/ን/አስ/ ደጋፍ የስራ ሂደት ባለው በታሸገ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. የመወዳደሪያ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ለዋጋ መስጫ በተዘጋጀው ቦታ ያለ ቫትና ከቫት ተለይተው መስጠት ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ ሁለት ቀናት በፊት ኦርጅናል እና ደረጃቸውን የጠበቁ ናሙና በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 04 ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ሜዲካል ዳይሬክተር ቢሮ አጠገብ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
7. የጨረታው ሳጥን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣበትን 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአሥረኛው ቀን በ11፡00 ሰዓት ታሽጎ በቀጣዩ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በመንግስት ስራ ቀን ሆኖ ሰዓቱ እንደተጠበቀ ይሆናል፡፡ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታ ሳጥን መክፈቻ ሥነ- ስርዓትን አያጓትትም።
8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ጤና ጣቢያ ግዥ/ን/ጠ/አገ/የስራ ሂደት፡፡ 4ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁ 403
አድራሻ ፡- 0113692872 መካኒሳ አቦ መዞሪያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ /ፒስ ህንጻ / ወደ ውስጥ 400 ሜትር ገባ ብሎ ወረዳ 04 ጤና ጣቢያ
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-09-10
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአሥረኛው ቀን በ11፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-12 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአሥረኛው ቀን በ11፡00 ሰዓት ታሽጎ በቀጣዩ ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Lideta Sub City Woreda 04 Health Post
- Buyer address: ከሳር ቤት ዝቅ ብሎ በቫቲካን ኤምባሲ በሸጋ ምጣድ መግቢያ 500ሜ ገባ ብሎ የድሮ ፍርድ ቤት ጋር ወረዳ 04 መስተዳደር አዳራሽ ውስጥ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 503፡፡
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 120.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 31, 2026)
- Posted at: 2026-09-01T11:01:40.000Z