Textile, Garments and Uniforms
በን/ስ/ላ/ክ/ከ ፍሬህይወት ቁ.2 አጠቃለይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ እቃዎችንና አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Textile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather Products
Addis Ababa
More tags
StationeryOffice Supplies and ServicesCleaning and Janitorial Equipment and ServiceEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesSport Materials and EquipmentChemicals and ReagentsOffice FurnitureFurniture and FurnishingHouse FurnitureHand Tools and Workshop EquipmentMechanicalAmharic2merkatoFirehiwot No.2 Secondary & Preparatory School
Description
አንደኛ ዙር የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በን/ስ/ላ/ክ/ከ ፍሬህይወት ቁ.2 አጠቃለይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ እቃዎችንና አገልግሎቶች በግዥ መለያ ቁጥር 001/2019 ማለትም
- ሎት 01 ደንብ ልብስ፣
- ሎትዐ2 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
- ሎት 03 አላቂ የፅዳት እቃዎች፣
- ሎት 04 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- ሎት o5 የስፖርት እቃዎች፣
- ሎት o6 ኬሚካሎች
- ሎት o7 ቋሚ እቃና
- ሎት ዐ8 ጥገናዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ጨረታውን ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች
- ለሎት 01 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር)
- ለሎት ዐ2 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 9,000 (ዘጠኝ ሺህ ብር)
- ለሎት ዐ3 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 7,500 (ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር)
- ለሎት 04 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2,500 (ሁለት ሺህ አምስትመቶ ብር)
- ለሎት o5 የጨረታ ማስከበሪያ 6,350 (ስድስት ሺህ ሶስት መቶ ሃምሳ ብር)
- ለሎት o6 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 1200(አንድ ሺህ ሁለት መቶ ብር)
- ለሎት o7 የጨረታ ማስከበሪያ ( ብር 7,100 (ሰባት ሺህ አንድ መቶ ብር)
- ለሎት ዐ8 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 6,350 (ስድስት ሺህ ሶስት መቶ ሃምሳ ብር)
በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ (CPO) ከጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ፡
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ የቲንና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ በዘርፉ የተሰማሩ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ሰነዱን ከፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀን የሚቆይ ሲሆን በአስረኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ታሽጎ በተከታዩ የስራ ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ከት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት በተወዳደሩባቸው ለሎት 1፣ ለሎት 2፣ ለሎት 03፣ ለሎት 04 ፣ለሎት 05 እና ለሎት o6 ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ለሎት: 07 ማለትም ለቋሚ እቃ የፎቶ ናሙና ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት በፊትና ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም ፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- በን/ስ/ላ/ክ/ከ ፍሬህይወት ቁ.2 አጠቃለይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ወደ ሳሪስ
በሚወስደው ካዲስኮ ሕንፃ 100 ሜትር ገባ ብሎ ሲሆን ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር
011-442-49-34/011-440-13-04 ይደውሉ፡፡
የፍሬህይወት ቁ.2 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-10
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን 11፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-12 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ታሽጎ በተከታዩ የስራ ቀን 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Firehiwot No.2 Secondary & Preparatory School
- Buyer address: ሳሪስ ካዲስኮ ሕንፃ ከአስፋልት 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው በፍሬህይወት ቁ2 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 31, 2026)
- Posted at: 2026-09-01T11:26:22.000Z