Consumable Goods

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ እቃዎችን በሃራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቁያ ሃራጅ ጨረታ ቁጥር 06/2018/19 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ሸቀጣሸቀጥ(ልዩልዩ) ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣አዳዲስ አልባሳት፣ የኮንስትራክሽን ማቴሪያል፣ አዳዲስ አልባሳት (ጫማዎች) የኮንስትራክሽን ማቴሪያል(የቧንቧ እቃዎችን)፣ አዳዲስ አልባሳት(የመጋረጃ ጨርቆችን)፣አዳዲስ አልባሳት(የሱፍ ጨርቆች)እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎችን በሃራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዬጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et  ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን;-

በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-

1.ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፤ የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው ፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በኦከሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል። ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።

2.በ ተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም፡፡

3.የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት መመልከት ይቻላል።

4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሚወጣበት ቀን እና የሚያበቃበት እንዲሁም ሰዓት የሚያሳይ ሰንጠረዥ፡-

ተቁ

የእቃው አይነት

 

ጨረታው አይነት

 

በአዲስ ዘመን

የታተመበት ቀን

 

የጨረታው

የሚካሄድበት ቀን

 

ጨረታው

የሚጀመርበት ሰዓት

 

ጨረታው የሚከፈትበት ሰዓት

 

ስልክ ቁጥር

 

1

ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ)

 

ሃረጅ

25/12/2018

30/12/2018

 

4:00

 

8:00

 

0922 111 8429/022 211 8925

 

2

ኤሌክትሮኒክስ

 

ሃረጅ

25/12/2018

30/12/2018

 

4:00

8:00

 

0922 111 8429/022 211 8925

 

3

አዳዲስ አልባሳት

 

ሃረጅ

25/12/2018

30/12/2018

 

4:00

8:00

 

 

0922 111 8429/022 211 8925

4

አልባሳት(ጫማዎች)

 

ሃረጅ

25/12/2018

30/12/2018

 

4:00

8:00

 

 

0922 111 8429/022 211 8925

5

አዳዲስ አልባሳት (የመጋረጃ

ጫርቆች)

 

ሃረጅ

25/12/2018

30/12/2018

 

4:00

8:00

 

 

0922 111 8429/022 211 8925

6

ኮስሞቲክስ

 

ሃረጅ

 

25/12/2018

 

30/12/2018

 

4:00

8:00

 

0922 111 8429/022 211 8925

 

7

የኮንስትራክሽን

ማቴሪያል (የቧንባ ዕቃዎች)

 

ሃረጅ

 

25/12/2018

 

30/12/2018

 

4:00

8:00

 

0922 111 8429/022 211 8925

 

8

ያገለገሉ ሞተርሳይክሎች

 

ሃረጅ

 

25/12/2018

 

30/12/2018

 

4:00

8:00

 

 

0922 111 8429/022 211 8925

9

አዳዲስ አልባሳት(የሱፍ ጨርቆች)

 

ሃረጅ

 

25/12/2018

 

30/12/2018

 

4:00

8:00

 

 

0922 111 8429/022 211 8925

4.በጨረታው ሽያጭ የእቃዎቹ አስመጪ ቤተሰብ ወይም ባለቤት የሆኑ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም።

5. በሃራጅ ጨረታ ለምትወዳደሩ ለጨረታው ዋስትና የሚሆን ማለትም፤ ለምድብ 01, ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) ብር 77,800.00፣ለምድብ 02, ሸቀጣሸቀጥ(ልዩ ልዩ) ብር 33,300.00፣ ለምድብ 03, ሸቀጣሸቀጥ(ልዩ ልዩ) ብር 191,500.00 ፣ለምድብ 04, ኮስሞቲክስ ብር 406,400.00 ፣ለምድብ 05, የኮንስትራክሽን ማቴሪያል ብር 213,500.00፣ ለምድብ 06, ኮስሞትከስ ብር 849,300.00፣ ለምድብ 07, ኮስሞትከስ ብር 204,500.00 ፣ ለምድብ 08, የኮንስትራከሽን ማቴሪያል(የቧንባ እቃዎች) ብር 219,400.00፣ለምድብ 09, ኤሌከትሮኒክስ ብር 119,100.00፣፣ለምድብ 10, ኮስሞትክስ ብር 23,600.00፣ለምድብ 11, ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) ብር 127,100.00 ፣ለምድብ 12, አዳዲስ አልባሳት(የመጋረጃ ጨርቅ) ብር 3,915,400.00፣ለምድብ 13, አዳዲስ አልባሳት(የመጋረጃ ጨርቅ) ብር 1,985,000.00 ፣ለምድብ 14, ኤሌክትሮኒከስ ብር 64,000.00 ፣ለምድብ 15, ኮስሞትከስ ብር 15,000.00፣ ለምድብ 16, አዳዲስ አልባሳት(ጫማዎች) ብር 282,500.00፣17, አዳዲስ አልባሳት ብር 37,300.00 ለምድብ 18, ኮስሞትክስ ብር 2,500.00፣ ለምድብ 19,አዳዲስ አልባሳት(የሱፍ ጨርቆች)ብር 1,880,000.00 ፣ለምድብ 20,አዳዲስ አልባሳት(የሱፍ ጨርቆች) ብር 2,410,100.00 ለምድብ 21, ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ብር 25,000.00፣ ለምድብ 22, ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ብር 25,000.00፣ለምድብ 23, ያገለገሉ ሞተር ሳይከሎች ብር 25,000.00 እና፣ለምድብ 24, ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ብር 25,000.00በ(Customs Commission Adama Branch) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ ኦከሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።

6.በሃራጅ ጨረታ ለመሸጥ የወጡትን እቃዎች በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ በተከራየው የውርስ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 እንዲሁም ብዛቱ 556 ፓኬት አዳዲስ አልባሳት (የሱፍ ጨርቆች) በአዳማ ቆርቆሮ መ/ቤቱ አዲስ በተከራየው መጋዘን ቁጥር 3 ውስጥ ሚገኙ ሲሆን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 6 ስድስተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማየት እና መጫረት ይቻላል

7.በሃራጅ ጨረታ የእቃዎቹ የመነሻ ዋጋ ያልተወሰነላቸው ስለሆነ የመነሻ ዋጋ በተጫራች የሚሰጥ ይሆናል ።

8.አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 / ሶሰት/ የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

9.አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።

10.ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ ኢይችሉም፡፡

11.በጨረታው ሽያጭ የእቃዎቹ አስመጪ ቤተሰብ ወይም ባለቤት የሆኑ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም ተሳትፎ ቢገኝ በህግ ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡

12.በጨረታው ላይ የወጡት ሞተር ሳይክሎች ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ሳያስፈልገው በታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ብቻ በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ መጫረት ይችላል።

13.ከላይ በተ/ቁ 9 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

14.ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

15.ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን።

NB:- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁትን መረጃዎች ያላሟሉ ተጫራች ቢያሸንፍ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ሲፒኦ ለመንግስት ገቢ የሚደረግ እና እቃው በድጋሜ ጨረታ ላይ የሚወጣ መሆኑን እናሳውቃለን ። የኦክሸን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09- 05-11-5511/011-66-68-828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ለተጨማሪ መረጃ፡- አዳማ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት የመንግስት ጉምሩከ መጋዘን የስራ ሂደት ስልክ ቁጥሮች 0221118429 እና 0222118925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-05
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-05 14:00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Adama Custom Commission Branch Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 31, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T11:27:24.000Z
← Back to all tenders