Textile, Garments and Uniforms

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 1 ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎች መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 1 ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኙ ጽ/ቤቶች  ለ2019 የበጀት አመት 1ኛ ዙር ጥቅል ግዥ ግልፅ ጨረታ ለመፈፀም በስራ ላይ የሚውል የተለያዩ

  • ሎት 1. 6211 ደንብ ልብስ -120,000 ብር
  • ሎት 2, 6212 የጽህፈት መገልገያ የቢሮ ዕቃዎች- 70,000 ብር
  • ሎት 3 6213 ህትመት ስራዎች-23,500 ብር
  • ሎት 4 6214 የህክምና ዕቃዎች-2,000 
  • ሎት 5. 6215 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች-1,600 ብር
  • ሎት 6. 6218 የጽዳት መገልገያ እቃዎች-120,000 ብር
  • ሎት 7. 6219 ሌሎች የቢሮ እቃዎች 6000 ብር
  • ሎት 8. 6241 የተሽከርካሪ መኪና አልባሳት ጎማ እና የሞተር ሳይክል ጎማ -38,400 ብር
  • ሎት 9. 6243 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና-8,000 ብር
  • ሎት 10 6244 የቢሮ እቃዎች ጥገና-10,000 ብር
  • ሎት 9. 6256 የመኪና ኪራይ-30,400 ብር

በዚህም መሰረት በግልፅ ጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባችሁ

1) በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ እና ንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ መሆን ይኖርባቸዋል።

2) ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ የዕቃውን አይነት ስም የተመረተበት ሀገር የሞዴሉን ቁጥር የተመረተበትን ጊዜ ያካተተ መሆን ይገባዋል።

3) ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ ቫትን ጨምሮ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው መሙላት አለባቸው በተጨማሪ የጨረታ ሰነድ ገንጥሎ ማስቀረት የተከለከለ ነው።

4) ተጫራቾች የእቃውን ናሙና ከየዓይነቱ አንዳንድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣ የጨረታው ውጤት ከታወቀ በኋላ ያቀረቡት ናሙናዎች ለተሸናፊዎች ሲመለሱ የአሸናፊዎቹ ተጫራቾች ናሙና ግን አይመለስም

5) ግዥ ፈጻሚው አካል አሸናፊ ተጫራቾች በሚመረጡበት ጊዜ የሚገዛውን ዕቃ ወይም አገልግሎት መጠን እንደ አስፈላጊነቱ 20% መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል

6) ተጫራቾች የተጫረቱበትን ዕቃዎች ናሙና ወደም ሳምፕል ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል እንዲሁም ተጫራቾች በምታቀርቡት ናሙና ሳምፕል ላይ ምንም ዓይነት ማህተም ስልክ ቁጥር እና ሌሎች ምልክቶችን ማድረግ ከውድድር ውጭ ያደርጋል።

7) የጨረታ ማስከበሪያ በመሙላት ጠቅላላ ዋጋ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በገንዘብ ተወስኖ በየሎቱ በተጠቀሰው መሰረት ሲፒኦ /CPO/ በአቃቂ ቃሊቲ ከ/ከተማ ወረዳ 1 ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል በማሰራት በዋናው ወይም በኦርጅናል ሰነድ ውስጥ ማቅረብ አለባቸው፤

8) ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በየሎቱ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በግልፅ በመሙላትና የድርጅቱን ማህተም በሠነዱ ላይ በመምታት ኦርጅናሉንና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማድረግ ሁለቱንም ፖስታዎች በአንድነት በኢንቨሎፕ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታዊ 10 /አስር/ የሥራ ቀናት ዘወትር ሰዓት ለዚሁ ጨረታ ለማገልገል በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ በፋይናንስ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በመቅረብ ማስገባት ይችላሉ።

9) ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተረጋገጠ በኋላ በሚጫረቱት የጨረታ ዋጋ ላይ በመመስረት የሚመለስ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።

10) ተጫራቾች የማይመለስ ብር በየሎቱ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዝርዝር ጉዳዩን የያዘ ሰነድ ከጽ/ቤቱ መግዛት ይኖርባቸዋል

11) የግልፅ ጨረታ ሳጥን በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 04:00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 4:30 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ ጽ/ቤት ውስጥ በተዘጋጀው ክፍል ውስጥ ይከፈታል።

12) ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09-20-67-97-02 /09-47-38 58-72/ 09 21-56-63-04/ 09-43-17-50-61

13) መ/ቤቱ የተሻለ ዘዲ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

14) ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች በሚያመርቱት እቃ ላይ የድጋፍ ደብዳቤ በማቅረብ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ከሚያመርቱት እቃ ውጪ ከሆነ በደብዳቤው መስተናገድ አይችሉም።

አድራሻ - አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ወደ ደብረ ዘይት በሚወስደው መንገድ ከቤተሰብ መምሪያ አጠገብ ነው።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 1 ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-12
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 04:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-12 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 04:30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Akaki Kality Sub-city Woreda 1 FEDB
  • Buyer address: አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ደብረዘይት መንገድ ከቤተሰብ መምሪያ /ካውንስሊንግ/ ኣጠገብ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: በየሎቱ 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 31, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T11:58:42.000Z
← Back to all tenders