Textile, Garments and Uniforms
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የም/ባሌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በዞኑ ስር ለሚገኙ የመ/መስሪያ ቤቶች የተለያዩ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል
Textile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather Products
Oromia
More tags
StationeryOffice Supplies and ServicesCleaning and Janitorial Equipment and ServiceEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesBuilding and Finishing MaterialsConstruction and Water WorksSpare Parts and Car Decoration MaterialsOffice FurnitureFurniture and FurnishingHouse FurnitureTri Wheeler, Motorcycles and Bicycles PurchaseCarpets and CurtainsAmharic2merkatoEast Bale Zone Finance Office
Description
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የም/ባሌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በዞኑ ስር ለሚገኙ የመ/መስሪያ ቤቶች በ2019 ዓ.ም በጀት የመጀመሪያ ዙር ግዥ፤
- 1) የደንብ ልብስ ጫማ እና የስፌት አገልግሎት
- 2) የፅህፈት መሳሪያ፤
- 3) የፅዳት እቃ፣
- 4) አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
- 5) የግንባታ እቃዎች
- 6) የመኪና ጎማ እና ባትሪ፤
- 7) ቋሚ እቃ (ፈርኒቸርና ኤሌክትሮኒክስ)፤
- 8) የሞተር ሳይክሎች 150 cc እና ከዛ በታች፤
- 9) የቢሮ ውስጥ ምንጣፎችና ማስዋቢያ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የመወዳደሪያ መስፈርት
- የንግድ ምዝገባ ቁጥር ያለው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- የ2018 ግብርን ከፍሎ ያጠናቀቀ። የንግድ ፍቃዱን ለ 2019 የስራ ዘመን ያሳደሰ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ከግብር ክፍያ ነፃ ስለመሆኑ ማስረጃ ክሊራንስ ማቅረብየሚችል።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ብር በምስራቅ ባሌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ስም አሰርተው በእጃቸው ይዘው መቅረብ ሲኖርባቸው ከ (2 አመት) ወዲህ |አዲስ የተደራጁ ማ ራት ካደራጃቸው አካል የጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና ደብዳቤ በእጃቸው ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የተደራጁ ማህበራት ካደራጃቸው አካል ህጋዊ መህበር መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በህትመት (ሃርድ ኮፒ) ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ከምስራቅ ባሌ ዞን ገቢዎች መስሪያ ቤት የማይመለስ 300 ( ሶስት መቶ) ብር በመክፈል መግዛት ይችላል።
- ጨረታውን ተወዳድሮ ያሸነፈው የሚፈርመው ውል ለግማሽ አመት ወይም ለ 6 ወር እንደሚቆይ ማወቅ ሲኖርበት፤ይህንን አውቆ ውል ለመግባት ፍቃደኛ የሆነ።
- ጨረታውን ተወዳድሮ ያሸነፈው ተጫራች የውል ማስከበሪያ ከተሰጠው ትእዛዝ ውስጥ 10% CPO ለማስያዝ ፍቃደኛ የሆነ።
- የተለያዩ ተቀናናሽ ከፍያዎችን ማለትም የቲኦቲ እና ከቫት 15 % ግማሹን (7.5) ለመከፈል ፍቃደኛ የሆነ።
- ተጫራች ጨረታውን ማሸነፉ ከተገለፀ እና ትእዛዝ ከተቀበለ በኋላ ባሉት በተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ ምስራቅ ባሌ ዞን ገንዝብ ጽ/ ቤት ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተወዳዳሪዎች ለውድድር ሲቀርቡ ቴክኒካል ማስረጃቸውን ዋናውንና፤ ኮፒውን ለየብቻ በሰም አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራች ፋይናንሺያል ማስረጃ ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በሰም በማሸግ ሙሉ ሰነዱን፤የመወዳደሪያ ዋጋቸውን በጥንቃቄ በግልፅ በማስቀመጥ፤ ስም፣ ፊርማ፣ የስልክ ቁጥራቸውን ፣ የድርጅታቸውን አድራሻ ፣ማህተም ፣ በመሙላት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱ ማቅረቢያ ጊዜ የሚያበቃው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ 11ኛ (አስራ አንደኛው) የስራ ቀን ከጠዋቱ 3:00 ሲሆን፤ ጨረታው የሚከፈተው በዚያው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ተወዳዳሪዎች ህጋዊ ወኪሎች፤የግዥ ኮሚቴዎች፤ ባለበጀት መስሪያ ቤቶች ባሉበት በምስራቅ ባሌዞን ገንዘብ ጽ/ቤት፣ በግዢ ክፍል ቁጥር 8 ውስጥ በግልጽ ይሆናል።
- የጨረታ ሰነዱ የሚከፈትበት ቀን ባጋጣሚ የስራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ ዘግይቶ የሚቀርብ ማንኛውም የመወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፤ የዋጋ ማሻሻል አይቻልም።
- ተጫራቾች መጫረት የሚችሉት ባላቸው የንግድ ፍቃድ ዘርፍ ብቻ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል። ከንግድ ፍቃዳቸው ዘርፍ ውጭ መወዳደር አይችሉም።
- ገዥው መስሪያ ቤት የግዥውን መጠን በ20 ፐርሰንት ቀንሶ ወይም ጨምሮ ሊገዛ ይችላል።
- ገዥው መስሪያ ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የእቃ ሞዴል የመሙላት ግዴታ አለባቸው የሚያቀርቡትን እቃ ሞዴል ካልሞሉ ዋጋቸው ተቀባይነት አይኖረውም።
- አቅራቢዎች ሚገጣጠሙ የሚታሰሩ ንብረቶችን (ወንበሮች፡ሼልፎች ጠረጴዛዎች) አስተካክለው ገጥመው ለንብረት ክፍል ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
- የላፐቶፕ ኮምፒውተር ፡ አሸናፊ ተወዳዳሪ ለ1 ወር የሚቆይ የዋስትና ጊዜ መኖሩን አውቆ መወዳደር ይኖርባቸዋል። እቃው ቸግር ካለበት የመመለስ ግዴታ አለባቸው የውል ማስከበሪያቸውም የዋስትና ጊዜው ሲያበቃ የሚመለስ መሆኑን መገንዘብ ይጠበቅባቸዋል።
ማሳሰቢያ
- ተጫራች ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎችን ከጨረታ ሰነድ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።
- ለአቅራቢው ክፍያ የሚፈጸመው በውድድሩ መሰረት ጥራት ያለውን እቃ በተፈለገው ጊዜ፤ መጠን፤ ቦታ፤ አይነት ሲያቀርብ በግዥ ኮሚቴዎች በሚመለከታቸው _ ባለሙያ አካላት ታይቶ ርክክብ ከተደረገና ህጋዊ ደረሰኝ ከተቆረጠ ቦኋላ ይሆናል።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 10 37 30 81/ 09 13 81 00 62 / 09 17 55 77 27
/ 09 75 89 67 20 ደውለው ማጣራት ይችላሉ።
የምስራቅ ባሌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት፣
ጊኒር
Tender details
- Deadline: 2026-09-12
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 11ኛ (አስራ አንደኛው) የስራ ቀን ከጠዋቱ 3:00
- Bid opening: 2026-09-12 12:00
- Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 11ኛ (አስራ አንደኛው) የስራ ቀን ከጠዋቱ 3:30
- Region: Oromia
- Publishing entity: East Bale Zone Finance Office
- Bid bond: 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 31, 2026)
- Posted at: 2026-09-01T12:07:33.000Z