Food Items and Drinks

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ የተለያዩ ግዥዎችን ለመግዛት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ የተለያዩ ግዥዎችን ለመግዛት ስለምፈልግ

እነርሱም፦

  • ሎት 1/ ቀለብ
  • ሎት 2/ የምግብ ማጣፈጫ
  • ሎት 3/ የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች
  • ሎት 4 የትምህርት ቁሳቁስ
  • 5 / የመኝታ ቀሣቁስ እና
  • ሎት 6/ የአልጋ ቺፑድ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ማንኛውም

1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከሩይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የሚገስፅ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2 የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያመለክት የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የንግድ ፈቃዳቸውን በመያዝ ቀርበው የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከግ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት መግዛት ይችላሉ።

3 .ተጫራቾች የሩዲናንስ እና ቴክንካስ ዶክመንት ፖስታ በአንድ ፖስታ በማሽግ በፖስታው ላይ ማህቴም በማድረግ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የሰጡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ ማካተት አለማካተቱን ፋይናሻል ጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ላይ በግልፅ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አሥር ሺህ ብቻ) ዋስትና በባክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/ቼክ በሁሉም ሎቶች ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

6. የጨረታ ማስከበሪያ በሌላ ፖስታ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በሀገር ውስጥ በግዥናንብረት ኤጄንሲ ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

8. ጨረታውን ለማደናቀፍ የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ሆኖ ለወደፊትም በመንግስት ግዥ ጨረታ ውስጥ የማይወዳደር ስለሆነ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ከተከፈተ በኃላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁ ማንኛውምሁኔታዎችመለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውንአልወዳደርም ማለት አይችልም።

10. የጨረታው አሽናፊ ጨረታውን ማሸነሩ በፅሁፍ ከተገለፀለት በኃላ በ15 የሥራቀናት ውስጥ ለውል ማስከበሪያ 10% ሲፒኦ/ጋራንቲ በመያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም አለበት። ውሉን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ባይገባ /ባይፈጽም የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።

11. የጨረታው አሽናፊ የሆነ ድርጅት ወክሎ ውሉን የሚፈርም የድርጅቱ ባለቤት ሳይሆን ቀርቶ ተወካይ ከሆነ ህጋዊ ውክልና ኦርጅናልና የማይመለስ ኮፒ ይዞ መቅረብ አለበት።

12. ለጨረታው የውል ማስከበሪያነት ያስያዘው ገንዘብ አሸናፊው ተጫራች ግዴታውን በውሉ መሰረት ካልፈጸመ በውሉ ላይ በሚገልጸው ህግ መሰረት መ/ቤቱ ተፈፃሚ የማድረግ መብት አለው።

13. ተጫራቾች የሚገዙ ዕቃዎች የሚያቀርቡት የእያንዳንዱ ዋጋ ሞልተው የሚያቀርቡና በፋይናሻል በጨረታ ሰነዱ ላይ በሚገኘው ማቅረቢያ ፎርም /መሙያ/ ዝርዝር ውስጥ ብቻ መሆን አለበት።

14. ጨረታው ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከቆዩ በኋላ በ16ኛው ቀን የሥራ ቀን ከሆነ ልክ ከቀኑ 4፡00 ሳጥኑ ታሽጎ ልክ 4፡30 ተጫራቾችና ህጋዊ ወክሎታቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።

15. መ/ቤቱ የግዥውን መጠን 25% መጨመርና መቀነስ ይችላል።

16. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ጂንካ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0467752488 ይደውሉ፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ

መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-18
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከቆዩ በኋላ በ16ኛው ቀን ከሆነ ልክ ከቀኑ 4፡00
  • Bid opening: 2026-09-18 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከቆዩ በኋላ በ16ኛው ቀን ከሆነ ልክ ከቀኑ 4፡30
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: የደቡብ ኢትዮጵያ መንግስት መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ
  • Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺ ብር)
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Sep 01, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T14:15:52.000Z
← Back to all tenders