Software Provision, Development and Web Design
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ2019 በጀት ዓመት አንቲቫይረስ ለዴስክቶፕ ኮምፒውተር፣ ለላፕቶፕ ኮምፒውተርና ለሰርቨር ዩፒኤስ አገልግሎት የሚውል አንቲቫይረስ በግለጽ የጨረታ ማስታወቂያ ከአቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ኢሎአ /001/2019
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ2019 በጀት ዓመት አንቲቫይረስ ለዴስክቶፕ ኮምፒውተር፣ ለላፕቶፕ ኮምፒውተርና ለሰርቨር ዩፒኤስ አገልግሎት የሚውል አንቲቫይረስ በግለጽ የጨረታ ማስታወቂያ ከአቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ሁሉ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ መስከረም 4 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በዚህ ሥራ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመሰስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ስም በተከፈተ የባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000004652782 ገቢ በማድረግ ዋናውን ማስረጃ በማቀረብ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
ተጫራቾች በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ስም የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ሳይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ በማስያዝ ዋናውን ማስረጃ ከጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። ተጫራቾች የቴክኒካልና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዶቻችሁን የያዘ አንድ ዋና እና አንድ ቅጂ ሰነድ ለየብቻው በፖስታ በማሽግና በፅሁፍ በመለየት የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፤ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ከሊራንስ፤ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት፣ የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የሚገባበት ቅፅ እና የጨረታ ማስከበሪያውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ የመጫረቻ ስነዶቻቹሁን አሟልታችሁ እስከ መስከረም 4 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ አለሰባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት መስከረም 4 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና መ/ቤት ይከፈታል። አገልግሎቱ ስለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-126-7816 ደውሎ መረዳት ይቻላል።
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት
Tender details
- Deadline: 2026-09-14
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-09-14 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት
- Bid bond: 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 01, 2026)
- Posted at: 2026-09-01T14:30:54.000Z