Textile, Garments and Uniforms
የዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ማዕከል በ2019 በጀት ዘመን የተለያዩ ዕቃዎችን በሎት በመደብ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Textile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather Products
Oromia
More tags
Cleaning and Janitorial Equipment and ServiceConsumable GoodsAnimal FeedAgriculture and FarmingChemicals and ReagentsProducts and ServicesRaw Materials and SuppliesHouse and BuildingMaintenance and RepairConstruction Machinery and EquipmentConstruction and Water WorksEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsFood and BeverageFood Items and DrinksBuilding and Finishing MaterialsWater Pipes and FittingsSanitary and CeramicsPlastic ProductsPlastic Raw Materials and ProductsMaterialsEducation and TrainingAmharic2merkatoZiway Rehabilitation Dev't Correctional Center
Description
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ማዕከል በ2019 በጀት ዘመን የተለያዩ ዕቃዎችን በሎት በመደብ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- በሎት አንድ፡- የህግ ታራሚዎች የምግብ ሸቀጦች የተለያዩ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ፤ የፅዳት ዕቃዎች ፤ የእንስሳት መኖ፤ የተለያዩ የግብርና ኬሚካሎች እና የአትክልት ዘሮች ግዥ።
- በሎት ሁለት፡- ለቤቶች እድሳትና ጥገና የሚውሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽ ዕቃዎች የኤሌክትሪክና የቧንቧ ዕቃዎችና የቢሮ ውስጥ አነስተኛ መገልገያ ዕቃዎች ግዥ።
- በሎት ሶስት፡- ለትምህርትና ስልጠና የሚውሉ ዕቃዎች ፣ ለቤቶች እና ለመሰረተ ልማት ዕድሳት የሚውሉ የተለያዩ የኮንስትራክሽንና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ግዥ ናቸው።
ስለዚህ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በከፈለ ሰነዱን ዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ቤት ማዕከል ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 32 ከግዥ ክንውን ቡድን ክፍል በመግዛት በጨረታው ሰነድ ላይ የምትሸጡበትን ዋጋ በግለፅ በታሸገ ኤንቨሎፕ በሙላት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ሳጥን መዝጊያ የሶስቱም ሎት በ10ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይዘጋል።
- የሎት አንድ ጨረታ ሳጥን መክፈቻ 10ኛው የስራ ቀን 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- የሎች ሁለት ጨረታ ሳጥን መክፈቻ 10 ኛው የስራ ቀን 9፡00 ሰዓት ይከፈታል።
- የሎችሶስት ጨረታ ሳጥን መክፈቻ ከ11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል።
- የተገለፀው ቀን ካላንደር የሚዘጋው ሆኖ ከተገኘ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት የሚዘጋ እና የሚከፈት ይሆናል።
- ለመወዳደር የሚመጡ ተጫራቾች፡-
- የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ዋጋ ተመጣጣኝ የሆነ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ከኦርጅናል ጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አግባብነት ያለው የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርበታል።
- የዘመኑን የመንግስት ግብር ግዴታ መወጣታቸውን የሚገልፅ የድጋፈ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ የምስክር ወረቀት (ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች) ማቅረብ ይኖርበታል።
- በግዥ ኤጀንሲ ድረ-ገፅ (WWW.ppa.gov.et ) በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን ይኖርበታል።
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ናሙና የተጠየቀባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ግዴታ መሆኑን በማወቅ ዋጋ ተሞልቶ ናሙና አለማቅረብ የተከለከለ ነው።
- ለሚጫረቱት እቃ በዘርፉ የተገቡ መሆን አለባቸው።
- ከላይ እንደተገለፀው ጨረታው በማዕከሉ ቅጥር ግቢ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 32 ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046 441 4301 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን
በፌዴራል መረሚያ ቤት ኮሚሽን የዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ማዕከል
Tender details
- Deadline: 2026-09-12
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-14 10:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Oromia
- Publishing entity: Ziway Rehabilitation Dev't Correctional Center
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Sep 01, 2026)
- Posted at: 2026-09-01T15:00:48.000Z