Spare Parts and Car Decoration Materials
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ የተሽከርካሪ ጎማ ለ2 ዓመት በሚቆይ የማዕቀፍ ግዥ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: ደ/ም/ኢት/ህ/ክ/መ/ፋይ/ ቢሮ 001/2019
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ ለሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶች የሚሆን የተሽከርካሪ ጎማ ለ2 ዓመት በሚቆይ የማዕቀፍ ግዥ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
1. በመስኩ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክሰ ምዝገባ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ቢያንስ አንድ ዙር በመስኩ በመንግስት ግዥ ላይ በመሳተፍ በገቡት ውል መሰረት ስለማቅረባቸው የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋጋ የተሞላበትን ኦሪጅናልና ኮፒ በመለየት ፊርማና የድረጅቱን ማህተም በእያንዳንዱ ገጽ በማሳረፍ እና በፖስታ በማሽግ ጨረታው ይፋ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ድረስ ቦንጋ በሚገኘው የክልሉ ፋይ/ቢሮ ቁጥር 6 ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ዘግይቶ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 700 /ሰባት መቶ ብር/ በኢት/ን/ባንክ የክልሉ ፋይ/ቢሮ አካውንት ቁጥር 1000454348471 ላይ ገቢ በማድረግና ደረሰኙን በማቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
5.ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ይፋ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ ለ15 የሥራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ የተጫራቾች ያለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያስቀርም፡፡ 16ኛው ቀን የሰራ ቀን ሆኖ ካልተገኘ በሚቀጥለው የመንግስት የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
6. የጨረታ አሸናፊ የሆነ ተጫራች ጎማዎችን በራሱ ወጪ አጓጉዞ በክልል ክላስተር ከተሞች /ቦንጋ፤ ቴፒ፤ ተርጫ እና ሚዛን አማን ከተሞች አስመርምሮ ስለትክክለኛነቱ በማረጋገጥ ማስረከብ አለበት፡፡
7. ጨረታውን ያሸነፈው አቅራቢ የውል ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ውል ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 400,000 ብር /አራት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው፡፡
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- በጨረታው ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች በስ/ቁር 047 3311 888 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች
ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-09-19
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ይፋ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-19 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ይፋ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: South West Ethiopia Region
- Publishing entity: ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ
- Bid bond: 400,000 (አራት መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 700 (ሰባት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 02, 2026)
- Posted at: 2026-09-02T07:29:06.000Z