Transportation Service

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት የመኪና ኪራይ፣ የልጆች መጽሔት ህትመት፣ የዳይሬክተሪ ህትመት እንዲሁም የአክለሪክ ፎቶ ህትመት መግዛት ይፈልጋል

Description

የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በድጋሚ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡-ኢፕድ 004/2019

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጹትን አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ በውል ለአንድ ዓመት መግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፦

  • ሎት 1. የመኪና ኪራይ አገልግሎት ለአንድ ዓመት በውል
  • ሎት 2. የልጆች መጽሔት(ብላቴናት፣ ዳኢመን እና ኡበድሰን) ህትመት በውል ለአንድ ዓመት
  • ሎት 3. የዳይሬክተሪ ህትመት አንድ ጊዜ
  • ሎት 4. የአክለሪክ ፎቶ ህትመት በውል ለአንድ ዓመት

ስለሆነም፡- ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ።

1. በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ታከስ ክሊራንስና በመንግሥት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።

2. ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ገዥውን አስመልከቶ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት በመውሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ ከቫት ጋር በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በ4 የታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒዎቻቸውን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀው በአቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

3. ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር

  • ለሎት 1.ብር 100,000.00
  • ለሎት 2.ብር 50,000.00
  • ለሎት 3.ብር 50,000.00
  • ለሎት 4.ብር 50,000.00

በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /ቢድ ቦንድ ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ከአደራጃቸው አካል የሚሰጥ ዋስትና ደብዳቤ ማስያዝ አለባቸው።

4. ጨረታው ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በአቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አንደኛ ፎቅ በአቅርቦት መምሪያ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

5. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 011 1 56 98 69
ኢ.ሜይል [email protected] 
አድራሻ፡- አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-19
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-19 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Press Agency
  • Buyer address: አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 (አንድ መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Sep 02, 2026)
  • Posted at: 2026-09-02T08:03:25.000Z
← Back to all tenders