Veterinary Equipment and Supplies

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን በቀወት ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት ለቀወት ወረዳ እንስሳትና አሳ ሀብት ልማት ተ/ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ እንስሳት መድሃኒት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 002/2019

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን በቀወት ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት ለቀወት ወረዳ እንስሳትና አሳ ሀብት ልማት ተ/ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. እንስሳት መድሃኒት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው።

3. ተጫራቾች የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

4. ተጫራቾች የግዥው መጠን ከብር 200000 በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑበት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::

5. ተጫራቾች ከ1-5 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ::

6. ተጫራቾች የጨረታው ውድድር በጥቅል መሆኑን አውቀው ጨረታውን መሙላት ይጠበቅባቸዋል።

7. ተጫራቾች ለእያንዳንዳቸው ብር 20000 (ሃያ ሺ ብር) ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ሰነዱ ፀንቶ ከሚቆይበት 45 ቀን በኋላ ለተጨማሪ 28 ቀን ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን አውቀው የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቀባቸዋል።

9. ተወዳድረው የሚያሸንፉ ተጫራቾች 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መዋዋል የሚጠቀባቸው ሲሆን አቅርቦቱን ላከናወኑበት ክፍያ ሲጠይቁ በስማቸው የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለው ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

10. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይቻላል::

11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው 11ኛው ቀን ከጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛው እለት ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል። ነገር ግን ጨረታ የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 033-664-16-12 ማግኘት ይችላሉ::

የቀወት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

ሸዋሮቢት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-12
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው 11ኛው ቀን ከጠዋት 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-12 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው 11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Kewet Woreda Finance Office
  • Bid bond: 20,000.00 ብር ለእያንዳንዳቸው
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Sep 02, 2026)
  • Posted at: 2026-09-02T10:11:00.000Z
← Back to all tenders