Office Furniture

በሸገር ከተማ በገላን ክፍለ ከተማ የገላን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በገላን ወረዳ አስተዳደር ስር ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የቢሮ የፅህፈት መሳሪያዎችን፣ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎችን፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን፣ የፅዳትና አላቂ የቢሮ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር ገ/ወ/ገ/ፅ/ቤት 002/2019

በሸገር ከተማ በገላን ክፍለ ከተማ የገላን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በገላን ወረዳ አስተዳደር ስር ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ፣ የቢሮ የፅህፈት መሳሪያዎችን፣ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎችን፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን፣ የፅዳትና አላቂ የቢሮ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ፣

1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ የግብር መለያ ቁጥር እና የመንግስት ግብር ለመክፈላቸው ከግብር ሰብሳቢው መስሪ ቤት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማቅረብ የሚችሉ።

3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት አንስቶ ለ15 /ለአስራ አምስት/ የስራ ቀናት ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በገላን ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ሲንቄ ባንከ ቁጥር 106479370123 በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከገላንወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋጋ በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው /አስራ ስድስተኛው/ የስራ ቀናት በገላን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ከረፋዱ እስከ 4፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታው በአስራ ስድስተኛው የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከረፋዱ 4፡30 በገላን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ሆኖም ጨረታው በሚከፈትበት ሰዓት ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም።

6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚውል በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ሲፒኦ/ ብቻ ለቢሮ ፅህፈት መሳሪያዎች 30,000 /ሰላሳ ሺህ/ ለቢሮ ቋሚ ፈርኒቸር 20,000 /ሀያ ሺህ/ ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 30,000 /ሠላሳ ሺህ/ ለቢሮ ፅዳት እና አላቂ እቃዎች 20,000 /ሀያ ሺህ /ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

8. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ዝርዝር መሰረት ሞልተው መመለስ ይኖርባቸዋል እንዲሁም ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ናሙና /sample/ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝመብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፦ 0913321839/ 0910742350/ 0911827152

በገላን ክፍለ ከተማ የገላን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-21
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት አንስቶ በአስራ ስድስተኛው የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-21 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት አንስቶ በአስራ ስድስተኛው የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Gelan City Administration FEDB
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 400.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Sep 03, 2026)
  • Posted at: 2026-09-03T07:39:12.000Z
← Back to all tenders