House, Building and Warehouse
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት መሠረት ተጫራቾችን አወዳድሮ በነጋ ቦንገር ህንፃ አካባቢ የሚገኙ ሱቆችን ለማከራየት ይፈልጋል
Description
በአዲስ አበባ ከተማ የኮርፖሬሽን ይዞታ በሆነውና በነጋ ቦንገር ህንፃ አካባቢ የሚገኙ ሱቆችን ለማከራየት የመጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢ.ግ.ስ.ኮ/ብግጨ/5/2018
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት መሠረት ተጫራቾችን አወዳድሮ በነጋ ቦንገር ህንፃ አካባቢ የሚገኙ ሱቆችን ለማከራየት ይፈልጋል።
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የመንግስትም ሆነ የግል ድርጅቶች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፣ የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ የቫት ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ የምዝገባ ሠርተፊኬት (TIN) እንዲሁም ከገቢዎች ጽ/ቤት ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችዘወትር በሥራ ሰዓት አዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ፋይናንስ ዘርፍ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
ጨረታው መስከረም 5/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ መስከረም 5/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ስነ-ሥርዓት ይከናወናል። ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፦ ስልክ 0949632090/0911912222
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-09-15
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-09-15 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Agricultural Business Corporation
- Buyer address: ከሳሪስ ፋፋ የምግብ አክሲዮን ማህበር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Sep 03, 2026)
- Posted at: 2026-09-03T08:08:47.000Z