Equipment and Accessories
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ የቤት ዕቃ፣ ኮንስትራክሽን፣ አልባሳት፣ እስፔርፓርት፣ የፅዳት ዕቃ፣ ምግብ ነክ እና ልዩ ልዩ በሀራጅ እና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and Accessories
Somali
More tags
IT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice Supplies and ServicesInterior Design Service and MaterialHome Appliance and SuppliesFurniture and FurnishingKitchen EquipmentTextile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsSpare Parts and Car Decoration MaterialsCleaning and Janitorial Equipment and ServiceFood Items and DrinksFood and BeverageBuilding and Finishing MaterialsConstruction and Water WorksConstruction Machinery and EquipmentOther SalesSales, Disposals and ForeclosureAmharic2merkatoEthiopian Revenue and Custom Commission Jigjiga Branch Bureau
Description
የግልፅ እና የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ
- የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣
- የቤት ማስዋቢያ፣
- የቤት ዕቃ
- ኮንስትራክሽን፣
- አልባሳት፣
- እስፔርፓርት፣
- የፅዳት ዕቃ፣
- ምግብ ነክ እና ልዩ ልዩ በሀራጅ እና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን እቃዎች 03/13/2018 ጀምሮ ሳምፕል በማየት አና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል፤
ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች --
- በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ስና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤
- ለሀራጅ ጨረታው 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማቅረብ የሚችል፤
- ለግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የሚያቀርበው የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ(5%) ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማቅረብ የሚችል፤
- ለሀራጅ ጨረታ ተጫራቹ የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ ራሱ ያቀርባል፤
- ለግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
- ተጫራቹ በጨረታ አሸንፎ የገዛውን እቃ ክፍያውን በ05 ቀናት ውስጥ መፈፀም አለበት፤
- እቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤
- በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤
- አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤
- ማንኛውም ተጫራች እቃዎቹን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው ርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፤
- ተጫራቹ እቃዎቹን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፤
- ተጫራች የሞሉትን የጨረታ ሰነድ ከ03/13/2018 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት የዕቃ አወጋገድ ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ05/13/2018 ዓ.ም 3:45 ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፤
- የሐራጅ ጨረታው የሚካሄደው 05/13/2018 ከጠዋቱ 4፡15 በመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፤
NB:- አሸናፊ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ ሳምፕል ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም::
በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-10
- Bid closing time: 10:15
- Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-09-10 10:15
- Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Somali
- Publishing entity: Ethiopian Revenue and Custom Commission Jigjiga Branch Bureau
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Published on: Addis Zemen (Sep 03, 2026)
- Posted at: 2026-09-03T08:16:08.000Z