Textile, Garments and Uniforms
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ የወረዳ 09 ፋይናንስ ፅ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ የወረዳ 09 ፋይናንስ ፅ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት ቀጥሎ የተጠየቀውን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡
1. በዘርፉ የተሰማራበት የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፡፡
2. ከመንግስት ግዥ እና ንብረት አስወጋጅ ኤጀንሲ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት፡፡
3. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት(TIN) የተጨማሪ እሴት ታክስና ቲኦቲ ተመዝጋቢ የሆነበት ማስረጃ ማቅረበ የሚችል፡፡
4. የጨረታ ማስከበሪያ CPO በየሎቱ በብር ሎት- ደንብ ልብስ 10,300፣ሎት- 2 የፅህፈት መሳሪያ እና አላቂ የቢሮ እቃዎች 35000፣ ሎት 3 የህትመት ስራዎች 8650፣ሎት-4 የፅዳት ዕቃዎች 25100፣ ሎት 5 የጓሮ አትክልት 1500.00፣ ሎት-6 የእንስሳት መድኃኒት 500፣ ሎት-7 ትራንስፖርት 14516፣ ሎት-8 መስተንግዶ 15000 ፣ሎት-9 የአዳራሽ ዲኮር ስራ 1,500.00 ፣ሎት -10 ቋሚ ንብረት ኤሌክትሮኒክስ ግዥ 10150 ሎት 11 ቋሚ ንብረት ጥገና 10000 ፣ሎት12 የጉልበት አገልግሎት ግዥ 6000 ሎት 13 የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማ ግዥ 9000 ሎት 14 ቋሚ ንብረት 9000 ሎት 15 የልብስ ስፌት 2000 ለንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ለወረዳ 09 ፋይናንስ ጽ/ ቤት በሚል በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች በመወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን በመጻፍ መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቧቸው ሰነዶች ሙሉ አድራሻቸውን በመጻፍ ፋይናንሻል ለዚሁ ባዘጋጀነው የዋጋ መሙያ ሰነድ የመጫረቻ ዋጋ ከነቫቱ የተሞላበት ኦርጅናሉ ፡ ኮፒውን እና ቴክኒካል ሰነድ (የንግድ ፈቃድ፣ቲን ነምባር ቫት CPO፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት የመሳሰሉት ሰነዶች ኦርጅናሉን የሚገልጽ) ለየብቻ ሰነዶችን በፖስታ ውስጥ በማሸግ በድርጅቱ ኃላፊ ወይም በተወካይ ተፈርሞበት የድርጅቱ ማህተም በሰነዶቹ እና በፖስታ ላይ በመምታት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች ሰነዳቸውን በሚሞሉበት ጊዜ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም በአጋጣሚ ተከስቶ ከሆነ ከላይ በኩል ፓራፍ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 300.00(ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ከን/ ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 09 ፋ/ጽ/ቤት 4ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 13 ቀርቦ መግዛት ይችላሉ፡፡
9. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ለሎት01 ለሎት02፣ለሎት03 ለሎት04፣ ለሎት 05 እና ለሎት 06 ሎት 13 ሎት 14 ናሙና ማቅረብ አለባቸው ፡፡ ለሎት 10 ማለትም ለኤሌክትሮኒክስ እቃ የወረዳው የፍላጎት መግለጫ መሰረት ብቻ ይሆናል
10. ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 29/12/2018 ዓ.ም እስከ 8/01/2019 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
የጨረታ ሳጥን በ08/01/2019 ዓ.ም በ11፡30 ሰዓት ታሽጎ 11/01/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
11. መስሪያ ቤቱ በግዥ ዝርዝር ከቀረበው የእቃ ብዛት ላይ 20% መቀነስና መጨመር መብት አለው፡፡
12 ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ለመስሪያ ቤቱ ያቀርባሉ፡፡
13.መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ- ሳሪስ አዲስ ሰፈር
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ 011 888 6813/011 888 6814
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-18
- Bid closing time: 17:30
- Bid opening: 2026-09-21 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Nifas Silk Lafto Sub City Woreda 9 Finance Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 04, 2026)
- Posted at: 2026-09-04T07:34:51.000Z