Textile, Garments and Uniforms

በአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ ወረደ 14 ህዳሴ ቅ/መጀ የመጀ/ደ/ት ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ ወረደ 14 ህዳሴ ቅ/መጀ የመጀ/ደ/ት ቤት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።

1 ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

3. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው።

4. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

የሎት ቁጥር

 

የሎት ዝርዝር

 

የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጲያ ብር

የሎት ቁጥር

 

የሎት ዝርዝር

 

የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጲያ ብር

ሎት 1

ደንብ ልብስ

9100

ሎት 6

የቢሮ ቋሚ እቃዎች

8500

ሎት 2

አላቂ የፅዳት እቃዎች

9000

ሎት 7

ስፖርት እቃዎች

6500

ሎት 3

አላቂ የቢሮ እቃዎች

9870

ሎት 8

የላቦራቶሪ እና ህክምና እቃዎች

7283

ሎት 4

አላቂ የትምህርት እቃዎች

9200

ሎት 9

የግንባታ እቃዎች

3500

ሎት 5

ኤሌክትሮኒክስ

9500

ሎት 10

የህትመት ዕቃዎች

3000

ሁሉንም ሎቶች ለሚገዙ 75453.00 ብር (ሰባ አምስት ሺህ አራት መቶ ሀምሳ ሶስት ብር)

6. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአንድ ሎት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 3 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።

7. ተጫራቶች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ በየሎቱ የተዘጋጀውን የዋጋውን CPO በማካተት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

8. ጨረታው በአስረኛው (10ኛው) ቀን 11፡30 ሰአት ታሽጎ በቀጣይ የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

9. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና ማቅረብ ለማይችሉት ቋሚ እቃ በፎቶ የተደገፈ መረጃ ማቅረብ አለባቸው።

10. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት የት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።

11. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፋበትን እቃ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

አድራሻ፡- ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ በስተጃርባ እንገኛለን

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 639 4253
በአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ ወረደ 14 ህዳሴ ቅ/መጀ የመጀ/ደ/ት ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-15
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው (10ኛው) ቀን 11፡30 ሰአት
  • Bid opening: 2026-09-16 08:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው (10ኛው) ቀን 11፡30 ሰአት ታሽጎ በቀጣይ የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ሰአት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Hedase Kindergarten & Elementary School
  • Buyer address: ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በስተጃርባ እንገኛለን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: ለአንድ ሎት 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 04, 2026)
  • Posted at: 2026-09-04T08:14:23.000Z
← Back to all tenders