Textile, Garments and Uniforms

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለወረዳው የሚያስፈልጉ የተለያዩ ግብዓቶችን በተለያዩ ሎቶች አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሠራት ይፈልጋል

Description

የ1ኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለወረዳው የሚያስፈልጉ የተለያዩ ግብዓቶችን በተለያዩ ሎቶች

  • ሎት1፡-የደንብ ልብስ፣
  • ሎት2፡ የፅህፈት መሣሪያዎች፤
  • ሎት3፡-የፅዳት እቃዎች፤
  • ሎት4፡-የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤
  • ሎት5፡ የፈርኒቸር እቃዎች፤
  •  ሎት6፡ ልዩልዩ መሣሪያዎች፤
  • ሎት7፡-መስተንግዶ፤
  • ሎት8፡ ልዩ ልዩ የኪራይ ዕቃዎች፤
  • ሎት9፡ የህትመት ሥራዎች፤
  • ሎት 10፡ የትራንስፖርት አገልግሎት፤
  • ሎት11፡-የደንብልብስ ስፌት፤
  • ሎት 12፡-የሠራተኞች መዝናኛ ክበብ (ካፍቴሪያ) አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሠራት ይፈልጋል።

ስለሆነም በዚህ ሥራ ላይ የተሰማራችሁ ነጋዴዎች አቅራቢዎች፤ አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች ሕጋዊ  ውክልና ያላችሁ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ በአካል ቀርባችሁ መወዳደር እንደምትችሉ እንገልፃለን።

በጨረታው ለመሳተፍ ለመወዳደር የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

  1. ሕጋዊ ንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፤
  2. የ2018 የመንግሥት ግብር የከፈለ ክሊራንስ ያለው እና የ2018 የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፤
  3. VAT ተመዝጋቢ የሆነ፤
  4. በመንግሥት ግዥዎች በአቅራቢነት የተመዘገበበትን መረጃ ማቅረብ የሚችል፤
  5. የተፈለገውን የተለያዩ አላቂና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ በአንድ ጊዜ ማቅረብ የሚችል፤
  6. በተባለበት ቦታና ቀን እቃውን የመሥሪያ ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ የሚችል፤
  7. በሥራና ክህሎት የተደራጃችሁ ኢንተርፕራይዙ በተደራጁበት የሥራ ዘርፍ ላይ ብቻ ልዩ ድጋፍ የሚያደርግላቸው ሲሆን ይህም የሚደረገው ከአደራጃቸው ጽ/ቤት ኃላፊ ብቻ በተፈረመ የድጋፍ ደብዳቤ ይሆናል። ከሥራ ዘርፉ ውጭ ለሆኑት እንደማንኛውም ነጋዴ የሚስተናገዱ ይሆናል።
  8. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር በእያንዳንዱ ሎት 500 (አምስት መቶ ብር) ከፍሎ መግዛት የሚችል፤
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ለሚጫረቱበት ሎት1፡-ብር 36,000 (ሰላሳ ስድስት ሺህ)፤ ሎት2፡-ብር 34,000 (ሰላሳ አራት ሺ)፤ ሎት፡-3 ብር 36,000 (ሰላሳ ስድስት ሺህ)፤ ሎት 4፡-ብር 30,000 (ሰላሳ ሺ)፤ ሎት 5፡-ብር 30,000 (ሰላሳ ሺ)፤ ሎት 6፡-ብር 5,000 (አምስት ሺ)፤ ሎት 7፡-ብር 22,500 (ሃያ ሁለት ሺ አምስት መቶ)፤ ሎት 8፡-ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺ)፤ ሎት 9፡-ብር 20,000 (ሃያ ሺ)፤ ሎት 10፡-ብር 20,000 (ሃያ ሺ)፤ሎት 11፡-ብር 10,000 (አስር ሺ)፤ ሎት 12 ብር 20,000 (ሃያ ሺ) የኢትዮጵያ ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ በጨረታው ሰነድ የመጀመሪያ (ቅድመ) ምርመራ  ውድቅ ይሆናል።
  10. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ እስከ መ/ቤቱ ግምጃ ቤት /ንብረት ክፍል/ ድረስ የመጓጓዣና የመገጣጠሚያ ዋጋ አካትተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  11. የዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች መረጃዎች የያዘው የጨረታ ሰነድ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ ሥራዎች፤ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርበታል።
  12. የጨረታ ማስገቢያ ቦታ ለሚ ኩራ/ክ/ከ/ወ/04/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 302 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  13. ጨረታውን ለመገምገም በሥራ ላይ የሚውሉትን ዘዴዎች ለዚሁ ግምገማ የሚያገለግሉትን መስፈርቶች እና እያንዳንዱ መስፈርት የሚኖረውን ድርሻ እንዲሁም ሁለት እና ከሁለት በላይ የሆኑ ዕጩ ተወዳዳሪዎች በግምገማ እኩል በሆኑ ጊዜ አሸናፊን ለመለየት በግዥ መመሪያው መሠረት የሚለይ ይሆናል።
  14. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው እራሳቸው ማግለል አይቻልም።
  15. የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ግዥውን 10% በብር /ሕጋዊ CPO/ማስያዝ የሚችል።
  16. የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10(አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ብቻ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ባሻሌ 40/60 ኮንዶሚኒየም አለፍ ብሎ ቃጥላ ማርያም መግቢያ በግምት 100 ሜትር ገባ ብሎ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 302 መግዛት ይቻላል።
  17. ጨረታው በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተጫራቹ ሕጋዊ ወኪል በተገኘበት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ተጫራቹ /ሕጋዊ ወኪሉ/ ያለመገኘት የጨረታ አከፋፈት ላይ ተፅዕኖ አያመጣም።
  18. ውድድሩን ያሸነፈ ተወዳዳሪ ውድድሩን ማሸነፉ ከታወቀ ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀን ውስጥ በአካል ቀርቦ የውል ስምምነት መፈረም አለበት።
  19. የእያንዳንዱ ዕቃ ዋጋ 15% ቫትን ጨምሮ መሞላት ይኖርበታል።
  20. ናሙና ለተጠየቀባቸው የዕቃ አይነቶች ተወዳዳሪዎች ምንም አይነት መለያ (ምልክት) ያልተደረገበት ለእያንዳንዱ እቃ አንድ ናሙና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዐ4 ፋይናንስ ጽ/ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  21. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ውድድሩን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ይሆናል።

ምርመራ አድራሻ፡- ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 በሻሌ 40/60 ኮንዶሚኒየም አለፍ ብሎ ቃጥላ ማርያም መግቢያ 100ሜ ገባ ብሎ።

በአዲስ አበባ ከተማ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር


Tender details

  • Deadline: 2026-09-16
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-16 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Lemi Kura Sub City Woreda 04 Administration Finance office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Sep 04, 2026)
  • Posted at: 2026-09-04T08:27:57.000Z
← Back to all tenders