Spare Parts and Car Decoration Materials

የድሬዳዋ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተለያዩ ዓይነት የመኪና ዕቃዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ላይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር ድ/ኤ/አ/ግ/ጨ/003/2019 ሎት-1 እና ሎት-2

የድሬዳዋ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በስሩ ለሚገኙ ተሸከርካሪዎች የሚውሉ የተለያዩ ዓይነት የመኪና ዕቃዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ላይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ሎት

የዕቃው ዓይነት

የጨረታ የመዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ

ሎት-1

 

የተለያዩ መጠን ያላቸው የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች

መስከረም 20 ቀን 2019 .400 ሰዓት፡፡

መስከረም 20 ቀን 2019 .430 ሰዓት፡፡

ብር 35,000.00(ሰላሳ አምስት ሺህ )

ሎት-2

የተለያዩ መጠን ያላቸው የተሽከርካሪ ባትሪዎች

መስከረም 20 ቀን 2019 .. 430 ሰዓት፡፡

መስከረም 20 ቀን 2019 .500 ሰዓት፡፡

ብር 15,000.00 (አሥራአምስት ሺህ )

  1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨ.እታ፣ የግብር ከፋይ መ /ቁጥር እና ከገቢዎች ባለሥልጣን ጽ/ቤት ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የሚል ማስረጃ ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
  2. ተጫራቾች የመንግሥት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ድረ-ገጽ ላይ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።
  3. በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሎት- 1. 800.00 (ስምንት መቶ) እና ለሎት 2 ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ በመከፈል መውሰድ ይችላሉ።
  5. ለድራሻ፡- ድሬዳዋ ግሪክ ካንፕ የድሬዳዋ ስታዲየም አጠገብ በሚገኘው የድሬዳዋ ኤሌክትሪክ አገልግሎት።
  6. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ከላይ በሠንጠረዡ ውስጥ በተገለፀው መሠረት ሆኖ በባንከ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ለስድስት ወራት የሚያገለግል የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ቴከኒካል “ኦርጅናል እና ኮፒ " እና ፋይናንሽያል “ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ድ/ኤ/አ/ግ/ጨ/003/2019 ከሎት-1 እና ሎት-2 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ሎት-1 እና መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ድረስ ሎት-2 ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ላይ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ሎት-1 እና ሎት 2 5፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል፣
  8. ጨረታው ከላይ በተገለጸው መሠረት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
  9. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡- 025-211-00-23/025 112 -98-45 በመደወል ወይም ቢሮ ቁጥር 204/205 በአካል በመቅረብ ማግኘት ይችላሉ።
  10. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የድሬዳዋ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-30
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-09-30 11:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: Dire Dawa Administration Electric Utility
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published on: Addis Zemen (Sep 04, 2026)
  • Posted at: 2026-09-04T08:44:47.000Z
← Back to all tenders