Textile, Garment and Leather
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የአቡራሞ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የአቡራሞ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብስ፣ የጽ/መሳሪያ ፤ መኪና ጎማ እና ኤሌክትሮኒክስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት የሚከተሉትን መስፈረቶች በጨረታ ሠነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የተጫራቾችን መመሪያ የሚያሟሉ ድርጅቶችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
1. በዘርፍ የተሰማሩበትን የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ
2. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው
3. የዘመኑ ግብር የከፈለ
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው
6. የጨረታውን ሠነድ በፌዴራል መንግስት ግዥ ንብረት ማስወገድ አዲስ አበባ ብር 500 ብር በመክፈል ጨረታው በአካባቢ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘውትር በሥራ ሰዓት ከጠዋት 2፡30 እስከ 11፡30 ሠዓት ድረስ በአካል ቀረበው መግዛት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የተጫረቱበትን የጨረታ ማስከበሪያ ለደንብ ልብስ 100,000/አንድ መቶ ሺህ ብር/፣ ለጽ/መሳሪያ 40,000/አርባ ሺህ ብር/ ፣ ለመኪና ጎማ 40,000/አርባ ሺህ ብር) እና ለኤሌክትሮኒክስ 25,000/ ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ከዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።
8. የገዙትን የጨረታ ሠነድ ማስታወቂያ ላይ ከወጣበት ከ5 ቀን ቦኃላ ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
9. ጨረታው ማስታወቂያ ላይ ከወጣበት ቀን ጅምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጧዋቱ 4፡00 ሠዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፌዴራል መንግስት ግዥ ንብረት ማስወገድ አዲስ አበባ ቢሮ ይከፈታል ዕለቱ የእረፍት ቀን አልያም የበዓል ቀን ላይ ከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
10. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ ንብረቶቹን የሚያሰረክቡበት ቦታ በቤ/ጉ/ክ/መ/በአቡራሞ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣትና ገቢ በማድረግ ከንብረት ክፍሉ በሚቀርበው የንብረት ገቢ ማድረጊያ ሞዴል 19 መሠረት ክፊያው የሚፈጸም ይሆናል።
11. ተጫራቾች ቴክኒካል ሠነድ አንድ ዋናው/ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በተለያየ ሦስት ፖስታዎች በማሽግ እንዲሁም ፋይናንሻል /የፋይኔሻል ሠነድ አንድ ዋናው/ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በተለያየ ሦስት ፖስታዎች በማሽግ ማስረጃ አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ እና ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ ማስረጃ በተለያዩ 3 ፖስታዎች በማሽግ በድምሩ 6ቱ ፖስታዎች በአንድ በማዘር ቦርድ ፖስታ በማድረግ ማስገባት ይኖርበታል።
12. ተጫራቾች ጨረታውን አሸናፊ ሊሆኑ የሚችለው በነጠላም ሆነ በጥቅል ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተወዳዳሪ የጨረታው አሸናፊ ሊያደረግ ይችላል።
13. መ/ቤቱ ከአሸናፊ ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በጨረታ ሠነዱ ላይ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በጨረታ ውድድሩ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር መጠን 20% ፐርሰንት መጨመር ወይም መቀነስ ይቻላል።
14. ዋጋ ማቅረብ የምትችሉት በገዛችሁት ሰነድ ላይ ብቻ ይሆናል ሙሉ የጨረታ ሰነዱ ማህተም ተመትቶ አብሮ መመለስ አለበት።
15. ለእያንዳንዱ ማለትም ለደንብ ልብስ፤ ለጽ/መሳሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ናሙና መቅረብ አለበት ለመኪና ጎማ እና ለኤሌክትሮኒክስ በቦታው ተገኝቶ ኮሚቴው ማየት ይችላል።
16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር +251 91 200 7671
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት የአቡራሞ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-22
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው ማስታወቂያ ላይ ከወጣበት ቀን ጅምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጧዋቱ 4፡00 ሠዓት
- Bid opening: 2026-09-22 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው ማስታወቂያ ላይ ከወጣበት ቀን ጅምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጧዋቱ 4፡30 ሠዓት
- Region: Beneshangul Gumuz
- Publishing entity: Assosa Zone Aburamo Woreda FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 04, 2026)
- Posted at: 2026-09-04T09:01:06.000Z