Textile, Garment and Leather

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ግብዓቶችን በግልጽ ጨረታ ግዥ ዘዴ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር በግልፅ ጨረታ ለወረዳው የሚያስፈልጉ የተለያዩ ግብዓቶችን በተለያዩ ሎቶች ሎት1.የደንብ ልብስ ሎት2.ሌሎች አላቂ ዕቃዎች ሎት3.የፅዳት ዕቃዎች ሎት4 የፕላንተ፣ለማሽነሪና ለመሣሪያ መግዣ እቃዎች ሎት5. ፈርኒቸር ግዥ ሎት6.የህትመት ስራዎች ሎት7. ትራንስፖርት አገልግሎት ሎት8.መስተንግዶ ሎት9. የደንብ ልብስ ስፌት ሎት10.ለፕላንተለማሽነሪ ጥገና ሎት11.የፈርኒቸር ጥገና ሎት12 የኪራይ ዕቃዎች ሎት13.የመኪና ጎማና የመኪና ዕቃዎች ሎት14 የጫኝና አውራጅ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ ግዥ ዘዴ አወዳድሮ ለመግዛት፣ አገልግሎትና ለመሥራት ይፈልጋል።

ስለሆነም በዚህ ስራ ላይ የተሰማራችሁ ነጋዴዎች/ አቅራቢዎች አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች/ ሕጋዊ ውክልና ያላችሁ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቱን የምታሟሉ በአካል ቀርባችሁ መወዳደር እንደምትችሉ እንገልጻለን።

በጨረታ መሳተፍ ለምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባችሁ፡-

1. ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው እና ቫትን ተመዘጋቢ የሆነ።

2. የ2018 የመንግስት ግብር የከፈለ ክሊራንስ ያለው እና የ2018 የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ ሚችል።

3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ህጋዊ ደረሰኝ ያላቸው እና በመንግስት ግዥዎች በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን መረጃ ማቅረብ የሚችል።

4. የተፈለገውን የተለያዩ አላቂና ቋሚ የቢሮ እቃዎች ሙሉ በሙሉ በአንድ ጊዜ ማቅረብ የሚችል።

5. በተባለበት ቦታና ቀን እቃውን ቢሮ ድረስ ማቅረብ የሚችል።

6. በስራና ክህሎት የተደራጃችሁ ኢንተርፕራይዙ በተደራጁበት የስራ ዘርፍ ላይ ብቻ ልዩ ድጋፍ የሚያደረግላቸው ሲሆን ይህም የሚደረገው ከአደራጃቸው ጽ/ቤት ኃላፊ ብቻ በተፈረመ የድጋፍ ደብዳቤ ይሆናል። ከስራ ዘርፍ ውጪ ለሆኑት እንደማንኛውም ነጋዴ የሚስተናገዱ ይሆናል።

7. ተጫራቾች የጨረታ የማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ(CPO)ለሚጫረቱበት ሎት 1. የደንብ ልብስ 30,000 /ሰላሳ ሺህ/ ብር ሎት 2. ሌሎች አላቂ ዕቃዎች 30,000 /ሰላሳ ሺህ/ብር ሎት 3. የፅዳት ዕቃዎች 25,000/ሃያ አምስት ሺህ/ብር ሎት 4. ለፕላንት ማሽነሪና መሣሪያ መግዣ 10,000 /አስር ሺህ/ብር ሎት 5. የፈርኒቸር ዕቃዎች 10,000 /አስር ሺህ/ብር ሎት 6. የህትመት ስራዎች 25,000/ሃያ አምስት ሺህ/ብር ሎት 7. ትራንስፖርት አገልግሎት 20,000 /ሃያ ሺህ/ብር ሎት8.የመስተንግዶ 20,000 /ሃያ ሺህ/ብር ሎት 9. የልብስ ስፌት 5,ዐዐዐ /አምስት ሺህ/ብር ሎት 10. ለፕላንት ማሽነሪ ጥገና 10,000 /አስር ሺህ/ብር ሎት 11. የፈርኒቸር ጥገና 10,000 /አስር ሺህ/ብር ሎት 12. የኪራይ ዕቃዎች 20,000 /ሃያ ሺህ/ብር ሎት 13. የመኪና ጎማ እና የመኪና እቃዎች ግዥ 5,000 /አምስት ሺህ/ብር ሎት 14. የጫኝና አውራጅ አገልግሎት 10,000/ አስር ሺህ/ ብር የኢትዮጵያ ብር ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ በጨረታው ሰነድ የመጀመሪያ(ቅድመ) ምርመራ ውድቅ ይሆናል።

8. ጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10(አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰአት እስከ ቀኑ አስራ አንድ/11፡00/ሰአት ድረስ ጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር በእያንዳንዱ ሎት 500.00/ አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 05 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።

9. ተጫራቾች በእያንዳንዱ እቃ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች መረጃዎች የያዘው የጨረታ ሰነድ ዝርዝር በመግለጽ በታሸገ ፖስታ ሰነዱን በኦርጅናልና ኮፒ በድርጅቱ ክብ ማህተም በማድረግና ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

10. የጨረታ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰአት ላይ ሳጥኑ ይታሸጋል ስለዚህ ሁሉም ተጫራቾች ሰነዳቸውን አስገብተው ማጠናቀቅ አለባቸው።

11. ተጫራቾች ያሸነፏቸውን እቃዎች ተወዳድረው ካሸነፉበት ናሙና ምንም ለውጥ ሳያደርጉ በራሳቸው ወጪ ጭነው የማቅረብና ደረጃውን ያልጠበቀ እቃ ከሆነ መልሰው ትክክለኛውን እቃ የማምጣት ግዴታ አለባቸው።

12. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ እስከ መ/ቤቱ ግምጃ ቤት /ንብረት ክፍል/ ድረስ መጓጓዣና የመገጣጠሚያ ዋጋ አካትተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

13. ጨረታውን ለመገምገም በሥራ ላይ የሚውሉትን ዘዴዎች ለዚሁ ግምገም የሚያገለግሎትን መስፈርቶች እና እያንዳንዱ መስፈርት የሚኖረውን ድርሻ እንዲሁም ሁለት እና ከሁለት በላይ የሆኑ ዕጩ ተወዳዳሪዎች በግምገማ እኩል በሆኑ ጊዜ አሸናፊን ለመለየት በግዥ መመሪያው መሰረት የሚለይ ይሆናል።

14. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይቻልም።

15. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ ጽ/ቤቱ ውስጥ ሲሆን፤ ጨረታው ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት በአል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል።

16. የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% /C.P.O/ በቅድሚያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

17. በማንኛውም ግልፅ ጨረታ ላይ ያልታገዱ መሆን አለበት።

18. የእያንዳንዱ እቃ ዋጋ 15 ቫትን ጨምሮ መሞላት ይኖርበታል።

19. ናሙና ለተጠየቀባቸው የዕቃ አይነቶች ተወዳዳሪዎች ምንም አይነት መለያ(ምልክት ያልተደረገበት ለእያንዳንዱ እቃ አንድ ናሙና በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው።

20. ውድድሩን ያሸነፈ ተወዳዳሪ ውድድሩን ማሸነፉ ከታወቀ ቀን ጀምሮ በ5(አምስት) ቀን ውስጥ በአካል ቀርቦ የውል ስምምነት መፈረም አለበት።

21. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ልዩ ስሙ ቦሌ አራብሳ ፕሮጀክት 15 ወይም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጀርባ 200 ሜትር ገባ ብሎ።

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-15
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰአት
  • Bid opening: 2026-09-16 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Lemi Kura Sub City Woreda 06 Finance Office
  • Buyer address: ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት ልዩ ስሙ ቦሌ አራብሳ ፕሮጀክት 15 ወይም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጀርባ 200 ሜትር ገባ ብሎ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Sep 04, 2026)
  • Posted at: 2026-09-04T09:18:51.000Z
← Back to all tenders