Textile, Garments and Uniforms

አፍሪካ ኅብረት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

አፍሪካ ኅብረት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ 2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን

  1.  ሎት 1 የደንብ ልብስ እና የስፌት ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 10000ብር
  2.  ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 9750 ብር
  3. ሎት 3 አላቂ የፅዳት እቃዎችየጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 8500 ብር
  4. ሎት 4 አላቂ የትምህርት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 9575 ብር
  5.  ሎት 5 ለሕትመት ስራ የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 1250ብር
  6. ሎት 6 የህንፃ ቁሳቁስ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 1975 ብር
  7. ሎት 7 የመስተንግዶ የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 886.45 ሳንቲም
  8. ሎት 8 የሽልማት ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 2500 ብር
  9. ሎት 9 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 9500 ብር

በዚህም መሠረት፡-

  1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድህረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ቼክ/ሲፒኦ/ ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በአፍሪካ ኅብረት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለጨረታ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል፡፡
  4.  ተጫራቾች ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ታሽጎ በአስራ አንደኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 በአፍሪካ ኅብረት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፣
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት/ እስከ ሎት 8 ናሙና ማቅረብ/ እና ሎት 9 ለቋሚ እቃዎች የፎቶ ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
  9.  አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚ መ/ ቤት ድረስ ማድረስ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10.  መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ት/ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት ግዥ ከፍል 20% ቀንሶ ወይም 20% ጨምሮ የመግዛት መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ተጫራቾች የሰነዳችሁን ዋጋ ስትሞሉ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት የለውም ::
  13. አሸናፊ ተጫራቾች የአሸነፉባቸውን ሎቶች ሲፒኦ 10% ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
  14.  አሸናፊ ተጫራቾች ለአሸነፉባቸው ዕቃዎች ጋራንቲ ዋስትና/ ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች የአንድ ዓመት ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

አድራሻ፡- በልደታ ክ/ከተማ ልደታ ጤና ጣቢያ ገባ ብሎ ወጣት ተሃድሶ ግቢ አጠገብ የት/ቤቱ ስልክ ቁጥር፡-

0115584665/ 0115581707/0118682457

የአፍሪካ ኅብረት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-16
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በአስረኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-17 10:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በአስራ አንደኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Africa Hibret Secondary School
  • Buyer address: በልደታ ክ/ከተማ ልደታ ጤና ጣቢያ ገባ ብሎ ወጣት ተሀድሶ ግቢ ውስጥ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 05, 2026)
  • Posted at: 2026-09-05T08:49:54.000Z
← Back to all tenders