Textile, Garment and Leather

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የደጃች ገነሜ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2019 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር 001/ 2018 ዓ.ም

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 የደጃች ገነሜ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2019 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ፦ ሎት 1፡-የደንብ ልብስ የስፖርት ትጥቅና የደንብ ልብስ ስፌት ሎት 2፡ -አላቂ የትምህርትና የቢሮ ዕቃዎች ሎት 3፡-የህትመት ስራዎች፤ ሎት 4፡-ሌሎች አላቂ ዕቃዎች (የፅዳት ዕቃዎችን)፤ ሎት5፡- ቋሚ ዕቃዎች እና የሊከትሮን መለዋወጫ፤ ሎት6፡-የፕላንት ማሽነሪ(ኤሌክትሮኒክስ) ጥገና ሎት7፡-ለህንፃ ቁሳቁስ (የውሀ መለዋወጫ የግንባታ ዕቃዎች)፤ ሎት8፡- ለመስተንግዶ የሚውል አቅርቦት እነዚህን ዕቃዎች እና ስራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር እንደሚችሉ ይጋብዛል።

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ በተሰጣቸው የንግድ ዘርፍ ብቻ መሳተፍ የሚፈልጉ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው።

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ያለው።

3. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ሊስት ላይ የተመዘገቡ መሆናቸው በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገፅ WWW.PPagOV.et ላይ መመዝገብ።

4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱትንና የሚመለከታችውን ማስረጃዎቸ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ሞልተው ሲመልሱ ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያዳንዱ ሎት የተጠቀሰውን ብር ከታወቀ ባንከ ስም በደጃች ገነሜ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ስም CPO በማሰራት ከዋናው የጨረታ ሰነድ ጋር ማስገባት ይኖርባችዋል።

ሎት

ሎት1

ሎት2

ሎት3

ሎት4

ሎት5

ሎት6

ሎት7

ሎት8

ብር

2,400

2,570

800

2,510

4,500

1,100

1,160

1,500

የውል ማስከበሪያ 10% ማሲያዝ ይጠበቅባቸዋል።

6. ተጫራቾች ለአሸነፉበት ዕቃ የሚፈፅሙት ማንኛውም ወጪ በራሳቸው በመሸፈን በሚሠጣቸው አሸናፊነት መሰረት ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው።

7. ተጫራቾች ማንኛውም የመንግሥት ታክሰና የግብር ግዴታዎች ከነማጓጓዣቸው በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ነጠላ ዋጋ ውሰጥ አካተው ማቅረብ አለባቸው።

8. ከላይ የተዘረዘሩትን መሥፈርቶቸ የሚያሟላ ተጫራች ካለ የማይመለስ ብር 400.00(አራት መቶ ብር) በመከፍል የተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ከት/ቤቱ ፋይናንስ ከፍል ቢሮ ቁጥር 04 መግዛት ይኖርባቸዋል።

9. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ (ሶስት) ቀን በፊት ለሚወዳደሩበት ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው ናሙና ለማይቀርብባቸው የዕቃ አይነቶች ስፔስፊኬሸን ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በግዢ አፈጻጸም መመሪያ ላይ ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተሰጠ ልዩ አስተያየትን ተግባራዊ ያደርጋል የጨረታ ሰነድ እያንዳንዱ ገጽ ላይ ማህተም እና ፊርማ በማድረግ መመለሰ ይኖርበታል። የጨረታው አሸናፊ አካል የውል ማሰከበሪያ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል:። መ/ቤቱ ለጨረታ ካቀረበው ዕቃ እሰከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ አንድ ኦሪጂናል ከአንድ ኮፒ ጋር ይህ ማስታወቂያ በአዲሰ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ት/ቤቱ በሚገኝበት አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አውቶቢስ ተራ ከፍ ብሎ በሚገኘው ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ አለባቸው።

11. ጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3:30 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት በዚሁ ቀን በትምህርት ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ከጠዋቱ 4:00 ላይ መገኘት በፈለጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መሰፈርቱን እስካሟሉ ድረሰ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታ ጨምሮ ጨረታው በእለቱ ይከፈታል። 11ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበአላት ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።

12.ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 011 213-7357/ 011 273 5974 በመደወል ማግኘት ይቻላል።

የደጃች ገነሜ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-17
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3:30
  • Bid opening: 2026-09-17 10:00
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Dejach Geneme Elementary School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 05, 2026)
  • Posted at: 2026-09-05T09:22:01.000Z
← Back to all tenders