Printing and Publishing
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አስተዳደር ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን አወዳድሮ አገልግሎት ለመፈጸም ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2019
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አስተዳደር ከዚህ በታች የተጠቀሰው የአገልግሎት ግዥ ለ2019 በጀት ዓመት አወዳድሮ አገልግሎት ለመፈጸም ይፈልጋል።
- ሎት 1. የህትመት ስራ አገልግሎት
- ሎት 2. የእንስሳት መድኃኒት ግዥ
ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋበዛሉ።
በዚህም መሰረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. አግባብነት ያለው የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ የቫት ተመዝጋቢዎች የሆኑ።
2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን በመገኘት የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚጫረቱበት የጨረታ ሎት ዓይነት ህትመት ስራ አገልግሎት 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) የእንስሳት መድኃኒት ግዥ 50,000 በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት አለባቸዉ።
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ሰነድ የስራውን ዝርዝር የሚገልጽ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻ ዋናውን (ኦርጅናል) እና የማይከፈት ኮፒ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ስምና አድራሻ በመጥቀስ የድርጅቱ ማህተም ያረፈበትን ፖስታ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን 4፡30 ላይ ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ በማግስቱ ባለው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ይከፈታል።
5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የነጠላ ዋጋ በሰነዱ ላይ በመግለጽ ሙሉ አድራሻና ማህተም መጠቀም አለባቸው።
6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-
1. ሙሉ ኦርጅናል የጨረታ ሰነድ ዋጋ ተሞልቶበት ህጋዊ ማህተም እና በየገፁ ፊርማ ተደርጐበት መመለስ አለበት። ካልተመለሰ ከጨረታ የሚሰረዝ መሆኑን እንገልጻለን።
2. የህትመት ስራ ሳምፕል መቅረብ አለበት።
አድራሻ፡- ቤተል ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አጠገብ ያለው ህንጻ ላይ
ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር
ዋና ስራ አስፈጻሚ ፑል የአስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02
ስልክ ቁጥር፡- 011 834-0979
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አስተዳደር
Tender details
- Deadline: 2026-09-17
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-17 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Kolfe Keranio Sub City Administration
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 05, 2026)
- Posted at: 2026-09-05T09:45:35.000Z
- Source: 2merkato