Chemicals and Reagents
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ሥር ለኩ አጠቃላይ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች፣ መድሃኒቶች፣ የህክምና ላቦራቶሪ ኬሚካሎች እና ሪኤጀንቶችን፣ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች እና የቢሮ ጽህፈት መሣሪያዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Chemicals and ReagentsLaboratory Equipment and ChemicalsCleaning and Janitorial Equipment and Service
Sidama
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ሥር ለኩ አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለተቋሙ ለህክምናና ለተለያዩ ሥራ ሂደቶች አገልግሎት ላይ የሚውሉ።
- 1ኛ) ለሆስፒታሉ የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች፣ መድሃኒቶች፣ የህክምና ላቦራቶሪ ኬሚካሎች እና ሪኤጀንቶችን
- 2ኛ) አላቂ የፅዳት ዕቃዎች
- 3ኛ) የቢሮ ጽህፈት መሣሪያዎችን
ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተዘረዘሩ ዕቃዎችን ሆስፒታሉ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚሁ መሠረት ተጫራቾች የሚከተሉትን ቅድመ ተከተል ሁኔታዎችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ
- የዘመኑን ማለትም 2019 የበጀት ዓመቱን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችል እዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር / TIN No / ያለው።
- ጨረታውን አሸንፎ የሚያቀርበውን ዕቃ ንብረት ጥራት ለማረጋገጥ ናሙና ማቅረብ የሚችል።
- ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ወይ አቅራቢ ዕቃውን /ንብረቱን እስከ ሆስፒታሉ በራሱ ወጪ የሚያቀርብ።
- አሸናፊ ሆኖ የሚጠራው ግለሰብ አቅራቢ ድርጅት የዕቃውን የንብረቱን ጥራት እና ደረጃ በጨረታ ሰነድ ላይ ሆስፒታሉ ባስቀመጠው መልኩ ውል ገብቶ በውሉ መሠረት የሚያቀርብ።
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት እና ቀናት የማይመለስ 300 /ሦስት መቶ/ ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከሆስፒታሉ ግፋን ዳይሬክቶሬት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ወይም በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ በግልፅ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታውን እዲያስገቡና በተገለፀው ቀን ከሆስፒታሉ ግፋን ዳይሬክቶሬት ለጨረታው በተዘጋጀ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዘርፍ ለእያንዳንዱ ጨረታ ማስከበሪያ 20,000 /ሃያ ሺህ / ብር ሲፒኦ (CPO) በመስሪያ ቤቱ ስም ለለኩ ሆስፒታል ማስያዝ ይኖርበታል።
- ጨረታው የሚገባበት ቀን ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ የሥራ ቀናት ተቆጥሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ እስከ 6፡30 ሰዓት ድረስ ለየዘርፉ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እዲያስገቡ ሆኖ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶችን ያላሟሉ ተጫራቾች ከውድድር ውጪ ይሆናሉ።
ማሳሰቢያ፡- ጨረታው የሚገባበት ቀን መደበኛ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀንና ሰዓት ይሆናል። ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 046-226-0373 ደውሎ መረዳት ይችላሉ።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የለኩ አጠቃላይ ሆስፒታል
Tender details
- Deadline: 2026-09-23
- Bid closing time: 12:30
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ እስከ 6፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-23 14:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የለኩ አጠቃላይ ሆስፒታል
- Bid bond: 20,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 05, 2026)
- Posted at: 2026-09-05T09:55:16.000Z