Food Items and Drinks
የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2019 ዓ.ም በመደበኛ በጀት በክልል ስር ለሚገኙ ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተማሪዎች አልሚ ምግብ ዱቄት /ፋፋ/ ግዥ ለመፈፀምና ለማጓጓዝ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ጨረታ ማስታወቂያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2019 ዓ.ም በመደበኛ በጀት በክልል ስር ለሚገኙ ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት የሚውል
- የተማሪዎች አልሚ ምግብ ዱቄት /ፋፋ/ ግዥ ለመፈፀምና ለማጓጓዝ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
- በየዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- በሚሳተፉበት አቅርቦት ጨረታ ከፍል አግባብ ካለው የመንግስት መ/ቤት ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ የአገልግሎት አቅርቦት እንደሚሰጡ የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ሠመራ ትም/ቢሮ ቁጥር 5 የጨረታውን ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ሀሳብ እና ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዶችን በመለየት በ2 ኮፒ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርበቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ትምህርት ቢሮ የዥ እና ንብረት አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ክፍል ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትምርት ቢሮ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 5 በ16ኛው የስራ ቀን በ3፡00 ሰዓት ይከፈታል።
- ለአሸናፊው ተጫራች የሚከፈል ቅድሚያ ክፍያ አይኖርም፤ በመሆኑም አቅርቦቱን በተገቢ ሁኔታ በስፔስፊኬሽን መሠረት አቅርቦቱን ማቅረቡ ሲረጋጋጥ 100% ከፍያ ወዲያው ይፈጸምለታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 5 ወይም በስልክ ቁጥር 033 666-0126/ 033-666-0123 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ /ሰመራ/
Tender details
- Deadline: 2026-09-22
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት
- Bid opening: 2026-09-23 09:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን በ3፡00 ሰዓት
- Region: Afar
- Publishing entity: Afar National Regional State Education Bureau
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 05, 2026)
- Posted at: 2026-09-05T10:00:34.000Z