Textile, Garments and Uniforms
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የምዕራብ አዲስ አበባ ሪጅን የሰራተኞች ደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት እና የጽዳት ዕቃዎች (ሳሙና እና ሶፍት) ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ላይ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ምዕ/አ/አ/ግ/ጨ/002/2019
የምዕራብ አዲስ አበባ ሪጅን በሪጅኑ ስር ለሚገኙ የሥራ ክፍሎች እና በአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለሚገኙ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች የሚውል የተለያዩ 6 (ስድስት) አይነት የሰራተኞች ደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት እና የጽዳት ዕቃዎች (ሳሙና እና ሶፍት) ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ላይ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ሎት |
የዕቃው አይነት |
የመዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የመክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ ዋስትና መስከበሪያ |
|
ሎት-1
|
የተለያዩ 6 (ስድስት) አይነት የሰራተኞች ደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት ግዥ |
መስከረም 09 ቀን 2019 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት
|
መስከረም 09 ቀን 2019 ዓ.ም 8፡30 ሰዓት |
ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) |
|
ሎት-2
|
ሳሙና እና ሶፍት |
ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ) |
1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨ.እ.ታ፣ የግብር ከፋይ መ/ ቁጥር እና ከገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የሚል ማስረጃ ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
2. ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ድህረ-ገፅ ላይ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።
3. በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር ለያንዳንዱ ሎት 400.00 (አራት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000150198667(EEU WAAR CU CON FOR EL CON) በሚለው ገቢ በማድረግ እና የከፈሉበትን የባንክ ስሊፕ ይዞ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
5. አድራሻ፡- ካዛንችስ አንድነት ፓርኪንግ 3ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የምዕራብ አዲስ አበባ ሪጅን ሰፕላይ ቼይን ግዥ እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ፣
6.ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ከላይ በሠንጠረዡ ውስጥ በተገለፀው መሠረት ሆኖ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በአንድ ላይ በማድረግ «ኦሪጅናል እና ኮፒ» በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ምዕ/አ/አ/ግ/ጨ/002/2019 ሎት -1 እና ሎት-2 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ መስከረም 09 ቀን 2019 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተራ ቁጥር 5 ላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን መስከረም 09 ቀን 2019 ዓ.ም 8፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፣
8. ጨረታው ከላይ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
9. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-127-9595/ 09 11 92 34 83 መደወል ይችላሉ።
10. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የምዕራብ አዲስ አበባ ሪጅን
Tender details
- Deadline: 2026-09-19
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-09-19 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Electric Utility
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 400.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Sep 06, 2026)
- Posted at: 2026-09-07T06:08:39.000Z
- Source: 2merkato