Vehicle and Machinery Sale

የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሣሪስ ሚችልኮትስ በሚገኘው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ አገልግሎት ዘርፍ ግቢ ውስጥ የሚገኙትን 57 ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችን፣ አንድ ባለ ሶስት እግር ባጃጅ እና ሁለት ሞተር ሳይክል በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ሣሪስ ሚችልኮትስ በሚገኘው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ አገልግሎት ዘርፍ ግቢ ውስጥ የሚገኙትን 57 ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችን፣ አንድ ባለ ሶስት እግር ባጃጅ እና ሁለት ሞተር ሳይክል በጨርታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው።

1. ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውንና የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 2000.00 /ሁለት ሺህ/ ብር በመክፈል ከጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 6፡30 እንዲሁም ከሠዓት ከቀኑ 7፡30 እስከ 11፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 6፡30 በቅሎ ቤት ከሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋ/መ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መግዛት ይችላሉ፤

2. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

3. ተጫራች ድርጅቶች አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው እንዲሁም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ማቅረብ አለበት።

4. ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ተጫርተው መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጅምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ቀርበው ማየት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ንብረት ብር 100,000.00 /መቶ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፤

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ሲሞሉ በግልጽ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ማሳየት አለባቸው፤

7. ጨረታው መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፤

8. የስም ማዘዋወሪያና ተያያዥ ክፍያዎች በአሸናፊው ተጫራች የሚከፈል ይሆናል።

9. አሸናፊው ተጫራች የመረከቢያ ሰነድ ወይም የሽያጭ ትዕዛዝ ደብዳቤ የሚሰጠው በጨረታ ላሸነፈበት መጠን በቅድሚያ ክፍያ ሲፈፅም ብቻ ነው።

10. ተጫራቾች በመወዳደሪያ ሰነዳቸው የድርጅታቸውን ስም፣ ፊርማ እና ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል፤ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው የተጫራቹን አጭር ፊርማ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፤

11. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የሰጡትን ዋጋ መለወጥም ሆነ ማሻሻል አይችሉም፤

12. የጨረታው አሸናፊ ተጫራች በጨረታው ያሸነፉትን ንብረት ሙሉ ክፍያ በ5 /አምስት/ የሥራ ቀናት በመክፈል ማንሳት ይኖርባቸዋል:: በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሳ ከ15ኛው ቀን በኋላ ላላነሳበት ቀን በየቀኑ ብር 100.00 /አንድ መቶ/ ቅጣት የሚከፍል ይሆናል።

13. አሸናፊው በራሱ ወጪ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ማስጫንና ማጓጓዝ አለበት።

14. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

15. ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0114-16-34-83 መጠየቅ ይቻላል።

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን

አድራሻ፦ በቅሎ ቤት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር 0114-16-34-83

አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-28
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid opening: 2026-09-28 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Trading Businesses Corporation
  • Buyer address: Addis Ababa, Ethiopia
  • Bid bond: 100,000.00 ብር
  • Bid document price: 2,000.00 ብር
  • Published on: Reporter (Sep 06, 2026)
  • Posted at: 2026-09-07T12:11:02.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders