Business, Industry and Factory Foreclosure

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. G+5 ሆቴል (ለንግድ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. (በቀድሞ ስሙ ደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ) ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን ከዚህ በታች በሠንጠረዡ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ሥልጣንና ውክልና መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የተበዳሪው ስም

የንብረት አስያዥ ስም

አበዳሪውቅርንጫፍ

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የቦታው ስፋት

የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር

የንብረቱ ዓይነት

የጨረታው መነሻ ዋጋ /ብር/

ጨረታ የሚከናወንበት

ከተማ

ቀበሌ

ቀን

ሰዓት

ሪኖ ዋን ትሬዲንግ /የተ/የግ/ማህበር

አበበች ለዲ ሲማ

ወሰን

ቢሾፍቱ

06/09

1088 ካሬ ሜትር

BI/10057/07

G+5 ሆቴል (ለንግድ)

 

139,505,191.68

04/02/2019 .

ከጠዋቱ 400-5:30

የጨረታ ደንቦች፡–

1.ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ ስም የተሰራ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) በማስያዝ መመዝገብ ይችላሉ።

2. የተጫራቾች ምዝገባ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል። በጨረታው የመጨረሻ ሰላሳ ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም።

3. ጨረታው ከላይ በሰንጠረዡ በተገለጸው ቀንና ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ይካሄዳል።

4. በጨረታው ላይ ተጫራቾች፣ አስያዥና ተበዳሪ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ።

5. የንግድ ማህበራትን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ ፅሁፍ የያዘና በማሀበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል።

6. የጨረታው አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ የተገለጸለት ተጫራች ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል። ባይከፍል ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል። ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል።

7. በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ እንዲሁም ብሔራዊ ባንክ ብድር ለማግኘት ያስቀመጣቸው አጠቃላይ መስፈርቶች ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ/አሸናፊ/ ባንኩ 70% (ሰባ በመቶ) ከፊል ብድር ያመቻቻል። ሆኖም ግን የጨረታው አሸናፊ በማንኛውም ሁኔታ መስፈርቱ ሳያሟላ በመቅረቱ ምክንያት ብድሩ ለጨረታው አሸናፊ ባይፈቅድ/ባይሰጥ የጨረታው አሸናፊ በተራ ቁጥር 6 ላይ የተመለከተው ግዴታ እና ሌሎች ግዴታዎቹን አያስቀርለትም።

8. በንብረት ማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈል ግብር፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የሊዝ ክፍያ ወይም ሌላ ማንኛውንም ክፍያ ገዢው ይከፍላል።

9. ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።

10. ለበለጠ ማብራሪያ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ዋናው መሥሪያ ቤት በስልክ ቁጥር 011 531 8117 (የህግ አገልግሎት መምሪያ) ወይም 011 668-0961 (ወሰን ቅርንጫፍ) ደውሎ መጠየቅ ወይም አበዳሪውን ቅርንጫፍ በአካል ቀርቦ ማነጋገርና ንብረቱን የሚጎበኙበት ሁኔታ ማመቻቸት ይቻላል።

11. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።


Tender details

  • Deadline: 2026-10-14
  • Bid closing time: 11:30
  • Bid opening: 2026-10-14 11:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Global Bank
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Reporter (Sep 06, 2026)
  • Posted at: 2026-09-07T13:04:43.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders